Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘፀአት 18:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ይትሮም እንዲህ አለ፦ “ከግብጽ እጅና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ፥ ከግብጽም እጅ በታች ሕዝቡን ያዳነ ጌታ ይባረክ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እንዲህም አለ፤ “ከግብጻውያን እጅና ከፈርዖን ለታደጋችሁ፣ ከግብጻውያን እጅ ሕዝቡን ለታደገ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 እንዲህም አለ፥ “ከግብጽ ንጉሥና ከሕዝቡም እጅ ያዳናችሁ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን! ሕዝቡንም ከባርነት ነጻ ያወጣ እግዚአብሔር ይመስገን!

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ዮቶ​ርም፥ “ከግ​ብ​ፃ​ው​ያን እጅና ከፈ​ር​ዖን እጅ ሕዝ​ቡን የአ​ዳነ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩክ ነው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ዮቶርም፦ ከግብፃውያንና ከፈርዖን እጅ ያዳናችሁ፥ ከግብፃውያንም እጅ ሕዝቡን ያዳነ እግዚአብሔር ይባረክ።

Ver Capítulo Copiar




ዘፀአት 18:10
16 Referencias Cruzadas  

አሒማዓጽም ጮኾ ንጉሡን፥ “ሁሉም ደህና ሆኖአል” አለ፤ ከዚያም ወደ መሬት ለጥ ብሎ በንጉሡ ፊት እጅ ነሣና፥ “በጌታዬ በንጉሡ ላይ እጃቸውን ያነሡትን ሰዎች አሳልፎ የሰጠ ጌታ አምላክህ የተመሰገነ ይሁን!” አለ።


ልዑል እግዚአብሔርም ይባረክ፤ ጠላቶችህን በእጅህ የጣለልህ። አብራምም ከሁሉ አሥራትን ሰጠው።


“የእስራኤል ጌታ አምላክ ይባረክ፤ ጐብኝቶ ለሕዝቡ ቤዛ አድርጎአልና፤


ኢየሱስ ክርስቶስ ከሙታን በመነሣቱ ሕያው የሆነውን ተስፋ የሰጠን፥ ከምሕረቱ ብዛት በአዲስ ልደት ልጆቹ ያደረገን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ እና አባት ይመስገን፤


በእናንተ የተነሣ በአምላካችን ፊት ለተደሰትነው ደስታ ሁሉ ስለ እናንተ ለእግዚአብሔር ምን ያህል ምስጋና ልናቀርብ እንችላለን?


በመንፈሳዊ በረከት ሁሉ በሰማያዊ ስፍራ በክርስቶስ የባረከን፥ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይባረክ።


እኔንም ስለ ቅንነቴ ደገፍከኝ፥ በፊትህም ለዘለዓለም አጸናኸኝ።


እንዲህም አላቸው፤ “የእስራኤል አምላክ ጌታ ይባረክ! ለአባቴ ለዳዊት የገባውን ቃል ኪዳን በአፉ እንደ ተናገረ፥ በእጁም ፈጽሙአል፤ እርሱም እንዲህ የሚል ነው፦


እንዲህም አለ፦ “ቸርነቱንና እውነቱን ከጌታዬ ያላራቀ የጌታዬ የአብርሃም አምላክ እግዚአብሔር ይመስገን፥ እኔ በመንገድ ሳለሁ እግዚአብሔር ወደ ጌታዬ ወንድሞች ቤት መራኝ።”


እርሱም ቄናውያንን፥ “ከእነርሱ ጋር እንዳላጠፋችሁ ከአማሌቃውያን ራቁ፤ ተለዩአቸውም፤ ምክንያቱም እናንተ እስራኤላውያን ከግብጽ ምድር በወጡ ጊዜ ቸርነት አድርጋችሁላቸዋልና” አላቸው። ስለዚህ ቄናውያን ከአማሌቃውያን ተለዩ።


ዳዊትም አቢጌልን እንዲህ አላት፤ “ዛሬ እንድታገኚኝ ወደ እኔ የላከሽ፥ የእስራኤል አምላክ ጌታ የተመሰገነ ይሁን!


“በገባው የተስፋ ቃል መሠረት ለሕዝቡ ሰላምን የሰጠ እግዚአብሔር ይመስገን፤ በአገልጋዩ በሙሴ አማካይነት ከሰጠውም መልካም ተስፋ ምንም የቀረ የለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios