ዘፀአት 18:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በአንድ ሰውና በጎረቤቱ መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክርክር በኖራቸው ቍጥር ጕዳያቸው ወደ እኔ ይመጣል፤ ለግራና ለቀኙ የሚሆነውን እኔ ወስኜ የእግዚአብሔርን ሥርዐትና ሕጎች እነግራቸዋለሁ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለት ሰዎች ተጣልተውም ወደ እኔ ቢመጡ የትኛው ወገን ትክክል እንደሆን ለማሳወቅ የእግዚአብሔርን ሕግና ሥርዓት እነግራቸዋለሁ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፤ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፤ የእግዚአብሔርንም ሥርዐትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገርም ቢኖራቸው ወደ እኔ ይመጣሉ፥ በዚህና በዚያ ሰውም መካከል እፈርዳለሁ፥ የእግዚአብሔርንም ሥርዓትና ሕግ አስታውቃቸዋለሁ አለው። |
በከተሞቻቸውም ከተቀመጡት ከወንድሞቻቸሁ ዘንድ ስለ ደም መፋሰስ ስለ ሕግና ስለ ትእዛዝ ስለ ሥርዓትና ስለ ፍርድም ማናቸውም ጉዳይ ወደ እናንተ ቢመጣ ጌታን እንዳይበድሉ፥ ቁጣም በእናንተና በወንድሞቻችሁ ላይ እንዳይመጣ አስጠንቅቁአቸው፤ እንዲህም ብታደርጉ በደለኞች አትሆኑም።
ሽማግሌዎቹንም፦ “ወደ እናንተ እስክንመለስ ድረስ በዚህ ቆዩን፤ አሮንና ሑርም እነሆ ከእናንተ ጋር ናቸው፥ ባለ ጉዳይም ቢኖር ወደ እነርሱ ይምጣ” አላቸው።
ሙሴም እስራኤልን ሁሉ ጠርቶ እንዲህ አላቸው፦ “እስራኤል ሆይ፥ እንድትማሩአት በማድረግም እንድትጠብቁአት ዛሬ በጆሮአችሁ የምናገራትን ሕግና ሥርዓት ስሙ።
ከዚህም በላይ እኔ ለእናንተ ከመጸለይ ወደ ኋላ በማለት ጌታን እንዳልበድል ይህ ከእኔ ይራቅ፤ እኔ መልካምና ቅን የሆነውን መንገድ አስተምራችኋለሁ።