ዘፀአት 18:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን ለመዳኘት ተቀመጠ፤ እነርሱም በዙሪያው ከጧት እስከ ማታ ድረስ ቆሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን በዳኝነት ለማገልገል ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በዙሪያው በመቆም አጨናንቀውት ከጠዋት እስከ ማታ ቈየ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም ሆነ፤ በነጋው ሙሴ በሕዝቡ ሊፈርድ ተቀመጠ፤ ሕዝቡም በሙሴ ፊት ከጥዋት እስከ ማታ ድረስ ቆመው ነበር። |
የሙሴ አማት ይትሮም የሚቃጠል ቊርባንና መሥዋዕትን ለእግዚአብሔር ወሰደ፤ አሮንና የእስራኤል ሽማግሌዎች ሁሉ በእግዚአብሔር ፊት ሊመገቡ ከሙሴ አማት ጋር መጡ።
የሙሴ አማትም ለሕዝቡ ያደርግ የነበረውን ሁሉ ባየ ጊዜ፦ “ለሕዝቡ የምታደርገው ይሄ ነገር ምንድነው? ሕዝቡ ሁሉ ከጥዋት እስከ ማታ በዙሪያህ ቆመዋል፥ አንተ ብቻህን ለምን ተቀምጠሃል?” አለው።