የፋሲካውንም መሥዋዕት እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቁርባን በምንቸትና በሰታቴ በድስትም ቀቀሉ፥ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።
ዘፀአት 12:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋውን በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ በእሳት የተጠበሰውን ካልቦካ ቂጣና ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋውንም በዚያችው ሌሊት በእሳት ላይ ጠብሰው ከመራራ ቅጠልና ከቂጣ ጋራ ይብሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥጋውንም በዚያኑ ሌሊት እየጠበሱ ከመራር ቅጠልና ካልቦካ ቂጣ ጋር ይብሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእሳትም የተጠበሰውን ሥጋውን በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ ቂጣውን እንጀራም ከመራራ ቅጠል ጋር ይብሉት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእሳት የተጠበሰውን ሥጋውንና ቂጣውን እንጀራ በዚያች ሌሊት ይብሉ፤ ከመራራ ቅጠል ጋር ይበሉታል። |
የፋሲካውንም መሥዋዕት እንደ ሥርዓቱ በእሳት ጠበሱ፤ የተቀደሰውንም ቁርባን በምንቸትና በሰታቴ በድስትም ቀቀሉ፥ ለሕዝቡም ሁሉ በፍጥነት አደረሱ።
ሙሴም ሕዝቡን አለ፦ ከባርነት ቤት ከግብጽ የወጣችሁበትን ይህንን ቀን አስቡ፥ ጌታ ከዚህ ቦታ በብርቱ እጅ አውጥቶአችኋልና ስለዚህ የቦካ እንጀራ አትብሉ።
ጌታም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈቀደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የጌታም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።