ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ ጌታ ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች፤ እንደ ቀድሞም ሆነች።
ዘፀአት 10:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አሁን እንግዲህ አንድ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፥ ይህንን ሞት ከእኔ እንዲያነሣልኝ ብቻ ጌታ አምላካችሁን ለምኑልኝ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ አሁን አንድ ጊዜ ደግሞ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝና ይህን ቀሣፊ መዓት እንዲያስወግድልኝ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑልኝ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህስ እነሆ፥ አንድ ጊዜ ብቻ በደሌን ይቅር እንድትሉኝ እለምናችኋለሁ፤ ይህን ከባድ ቅጣት ከእኔ እንዲያስወግድም አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑልኝ።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አሁን እንግዲህ እንደገና በዚህ ጊዜ ብቻ ኀጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ ወደ አምላካችሁ ወደ እግዚአብሔር ጸልዩልኝ” አላቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አሁን እንግዲህ በዚህ ጊዜ ብቻ ኃጢአቴን ይቅር በሉኝ፤ ይህንም ሞት ብቻ ከእኔ ያነሣልኝ ዘንድ አምላካችሁን እግዚአብሔርን ለምኑ አላቸው፤” |
ንጉሡ ኢዮርብዓም “እባክህ እጄን ያድንልኝ ዘንድ ወደ አምላክህ ወደ ጌታ ጸልይልኝ!” ሲል የእግዚአብሔርን ነቢይ ለመነው። የእግዚአብሔርም ነቢይ ወደ ጌታ ጸልዮለት የንጉሡ እጅ ዳነች፤ እንደ ቀድሞም ሆነች።
ፈርዖንም ሙሴንና አሮንን ጠርቶ “እንቁራሪቶቹን ከእኔና ከሕዝቤ እንዲያርቅ ወደ ጌታ ጸልዩልኝ፤ ለጌታም እንዲሠዋ ሕዝቡን እለቅቃለሁ” አላቸው።
ሕዝቡም ወደ ሙሴ መጥተው እንዲህ አሉት፦ “በጌታና በአንተ ላይ ስለ ተናገርን ኃጢአት ሠርተናል፤ እባቦቹን ከእኛ እንዲያርቅልን ወደ ጌታ ጸልይልን።” ሙሴም ስለ ሕዝቡ ጸለየ።