“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር ቢመጣ፥ በውርጭ፥ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ ቢትወረር፥ የሕዝብህም ጠላት የአገሩን ቀበሌዎች ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
ዘፀአት 10:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንበጣዎችም በግብጽ ምድር ሁሉ ላይ ወጡ፥ በግብጽም አገር ሁሉ ላይ ተቀመጡ፤ እጅግም ብዙ ነበሩ፥ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፥ ወደፊትም ደግሞ እንደ እርሱ ያለ አይሆንም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም ግብጽን በሙሉ ወረሩ፤ ስፍር ቍጥር የሌላቸው ሆነው የሀገሪቱን ዳር ድንበር ሁሉ አለበሱ። እንዲህ ያለ የአንበጣ መዓት ከዚህ ቀደም አልነበረም፤ ወደ ፊትም ደግሞ አይኖርም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም በመርመስመስ መጥተው አገሪቱን ወረሩ፤ ይህን ያኽል ብዛት ያለው የአንበጣ መንጋ ከዚያ በፊት ታይቶ አይታወቅም፤ ወደ ፊትም ሊታይ አይችልም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንበጣም በግብፅ ሀገር ሁሉ ላይ ወጣ፤ በግብፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀመጠ፤ እጅግም ብዙና ጠንካራ ነበር፤ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደ እርሱ አይሆንም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንበጣዎችም በግብፅ አገር ሁሉ ላይ ወጡ፤ በግብፅም ዳርቻ ሁሉ ላይ ተቀመጡ፤ እጅግም ብዙ ነበሩ፤ ይህንም የሚያህል አንበጣ በፊት አልነበረም፤ ወደፊትም ደግሞ እንደ እርሱ አይሆንም። |
“በምድሪቱ ላይ ረሀብ ወይም ቸነፈር ቢመጣ፥ በውርጭ፥ በዋግና በአንበጣ ወይም በኩብኩባ መንጋ ቢትወረር፥ የሕዝብህም ጠላት የአገሩን ቀበሌዎች ከብቦ ቢያስጨንቃቸው፥ መቅሠፍትና ደዌ ሁሉ ቢሆን፥
እነሆ እኔ ነገ በዚህ ጊዜ በግብጽ፥ ከተመሠረተች ቀን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እንደ እርሱ ያለ ሆኖ የማያውቅ፥ እጅግ ከባድ በረዶ አዘንባለሁ።