ዘፀአት 1:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮሴፍን የማያውቅ አዲስ ንጉሥ በግብጽ ተነሣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በግብጽም፣ ስለ ዮሴፍ የማያውቅ አዲስ ንጉሥ ነገሠ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ ሁሉ በኋላ ዮሴፍ ያደረገውን ነገር የማያውቅ አዲስ ንጉሥ በግብጽ ተነሣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በግብፅ ዮሴፍን ያላወቀ ሌላ ንጉሥ ተነሣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በግብም ዮሴፍን ያላወቀ አዲስ ንጉሥ ተነሣ። |
ሂድ የእስራኤልንም ሽማግሌዎች ትሰበስባለህ እንዲህም ትላቸዋለህ፦ “ጌታ የአባቶቻችሁ አምላክ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅ፥ የያዕቆብም ተገለጠልኝ፤ እንዲህም አለኝ ‘ጎበኘኋችሁ፥ በግብጽም የሚደረግባችሁን አየሁ፤
ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።