ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና።
ኤፌሶን 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጸጋው በእምነት አድኗችኋልና፤ ይህ የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ የመጣም አይደለም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእምነት፣ በጸጋ ድናችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ የዳናችሁት በእምነት አማካይነት በጸጋው ነው፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ በእናንተ ሥራ የተገኘ አይደለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምነን በጸጋው ድነናልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ጸጋ ነው እንጂ የእናንተ ሥራ አይደለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጸጋው በእምነት አድኖአችኋልና፤ ይህም የእግዚአብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም። |
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና።
ኢየሱስ መልሶ “የእግዚአብሔርን ስጦታና ‘ወሃ አጠጪኝ’ የሚልሽ ማን መሆኑን ብታውቂ ኖሮ፥ አንቺ በለመንሽው ነበር፤ የሕይወትም ውሃ በሰጠሽ ነበር፤” አላት።
እውነት እውነት እላችኋለሁ፤ ቃሌን የሚሰማ የላከኝንም የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፤ ከሞትም ወደ ሕይወት ተሻገረ እንጂ ወደ ፍርድ አይመጣም።
በደረሱም ጊዜ ቤተ ክርስቲያኑን ሰብስበው እግዚአብሔር ከእነርሱ ጋር ያደረገውን ሁሉ ለአሕዛብም የሃይማኖትን ደጅ እንደ ከፈተላቸው ተናገሩ።
ከትያጥሮን ከተማም የመጣች ቀይ ሐር ሻጭ እግዚአብሔርን የምታመልክ ልድያ ያሚሉአት አንዲት ሴት ትሰማ ነበረች፤ ጳውሎስም የሚናገረውን ታዳምጥ ዘንድ ጌታ ልብዋን ከፈተላት።
ስለዚህ በእምነት የሆነው፥ ተስፋው በእምነት እንዲያርፍና ለዘሩ ሁሉ እንዲሆን ነው፥ ይህም ሕግ ፈፃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአብርሃምን እምነት የሚጋሩትንም ጭምር ነው፥ እርሱ የሁላችንም አባት ነውና፥
እንደዚህ ያሉ ሰዎች ወደ ንስሓ መመለስ እንዴት ይቻላል!? አንድ ጊዜ ብርሃን የበራላቸው፥ ሰማያዊውንም ስጦታ የቀመሱ፥ ከመንፈስ ቅዱስም ተካፋዮች ሆነው የነበሩ፥