ኤፌሶን 1:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስም ለታመኑ፥ በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በእግዚአብሔር ፈቃድ የክርስቶስ ኢየሱስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፤ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉ፣ ለታመኑ፣ በኤፌሶን ለሚገኙ ቅዱሳን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነው ከጳውሎስ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ታማኞች ለሆኑት፥ በኤፌሶን ለሚገኙት ቅዱሳን፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእግዚአብሔር ፈቃድ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ ከሆነ ከጳውሎስ በኢየሱስ ክርስቶስ ላመኑ በኤፌሶን ላሉ ቅዱሳን፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ በኤፌሶን ላሉት ቅዱሳን በክርስቶስ ኢየሱስም ላሉት ምእመናን፤ |
እርሷም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፤” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን።
ነገር ግን ሲሰናበታቸው “የሚመጣውን በዓል በኢየሩሳሌም አደርግ ዘንድ ይገባኛል እግዚአብሔር ቢፈቅድ ግን ወደ እናንተ ደግሞ እመለሳለሁ፤” አላቸው። ከኤፌሶንም በመርከብ ተነሣ።
በእግዚአብሔር ለተወደዳችሁ፥ በሮሜ ላላችሁ ሁሉ፥ ቅዱሳን ልትሆኑ ለተጠራችሁ ከአባታችን ከእግዚአብሔር ከጌታም ከኢየሱስ ክርስቶስ ጸጋና ሰላም ለእናንተ ይሁን።
በዚህ ምክንያት የተወደደውንና የታመነውን በጌታ ልጄ የሆነውን ጢሞቴዎስን ልኬላችኋለሁ፤ በየስፍራው በአብያተ ክርስቲያናት ሁሉ እኔ እንደማስተምረው በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነው መንገዴን እርሱ ያሳስባችኋል።
በእግዚአብሔር ፈቃድ የኢየሱስ ክርስቶስ ሐዋርያ የሆነ ጳውሎስ፥ ከወንድማችንም ከጢሞቴዎስ፥ በመላው አካይያ ከሚኖሩ ቅዱሳን ሁሉ ጋር በቆሮንቶስ ላለች ለእግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፤
እናንተ ደግሞ በምን ሁኔታ እንዳለሁና እንዴት እንደምኖር እንድታውቁት የተወደደ ወንድምና በጌታ የታመነ አገልጋይ ቲኪቆስ ሁሉን ይነግራችኋል፤
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ናቸው።”
የሚጠብቅህን መከራ አትፍራ። እነሆ እንድትፈተኑ ዲያብሎስ ከእናንተ አንዳንዶቻችሁን በወኅኒ ሊያስገባ ነው፤ ለዐሥር ቀንም መከራን ትቀበላላችሁ። እስከ ሞት ድረስ የታመንህ ሁን የሕይወትንም አክሊል እሰጥሃለሁ።
“የት እንደምትኖር አውቃለሁ፥ የሰይጣን ዙፋን ባለበት ነው፤ ስሜንም ትጠብቃለህ፤ ሰይጣንም በሚኖርበት፥ በእናንተ ዘንድ የተገደለው የታመነው ምስክሬ አንቲጳስ በነበረበት ዘመን እንኳ በእኔ ያለህን እምነት አልካድህም።