መክብብ 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከሕያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሕያዋን መካከል ያለ ማንኛውም ሰው ተስፋ አለው፤ በሕይወት ያለ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሞተ አንበሳ ይልቅ በሕይወት ያለ ውሻ ይሻላል፤ በሕያዋን ምድር የሚኖር ሰው የተሻለ ተስፋ አለው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከሕያዋን ጋር አንድነት ያለው ማንም ሰው ተስፋ አለውና ከሞተ አንበሳ ያልሞተ ውሻ ይሻላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያልሞተ ውሻ ከሞተ አንበሳ ይሻላልና ሰው ከሕያዋን ሁሉ ጋር በአንድነት ቢኖር ተስፋ አለው። |
ለሁሉም አንድ ዓይነት ዕጣ ክፍል መኖሩ ከፀሐይ በታች በሚደረገው ነገር በሙሉ ይህ ክፉ ነው፥ ደግሞም የሰው ልጆች ልብ በክፋት ተሞልታለች፥ በሕይወታቸውም ሳሉ እብደት በልባቸው ውስጥ ይኖራል፥ ከዚያም በኋላ ወደ ሙታን ይወርዳሉ።