“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቆጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥
መክብብ 7:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምድር ላይ መልካምን የሚሠራ፥ ምንም ኃጢአት የማያደርግ ጻድቅ አይገኝምና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግና ፈጽሞ ኀጢአት የማይሠራ ጻድቅ ሰው በምድር ላይ የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምንም ስሕተት ሳይፈጽም ሁልጊዜ መልካም ነገርን የሚሠራ ደግ ሰው በምድር ላይ አይገኝም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በምድር ላይም መልካምን የሚሠራ ኀጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ ሰው አይገኝምና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በምድር ላይ መልካምን የሚሠራ ኃጢአትንም የማያደርግ ጻድቅ አይገኝምና። |
“መቼም በደል የማይሠራ የለምና ሕዝብህ ኃጢአት በመሥራት አንተን ሲያሳዝኑህ፥ አንተም ተቆጥተህ ጠላቶቻቸው ድል እንዲነሡአቸውና ወደ ሌላ አገር ማርከው እንዲወስዱአቸው በምትፈቅድበት ጊዜ፥ ምንም እንኳ ያ አገር ሩቅ ቢሆን፥
“ኃጢአት የማይሠራ ሰው የለምና በአንተ ላይ ኃጢአት ቢሠሩ፥ ተቈጥተህም ለጠላት አሳልፈህ ብትሰጣቸው፥ ሩቅም ወይም ቅርብ ወደ ሆነ አገር ቢማርኩአቸው፥
ሁላችን እንደ ርኩስ ሰው ሆነናል፥ ጽድቃችንም ሁሉ እንደ መርገም ጨርቅ ነው፤ ሁላችንም እንደ ቅጠል ረግፈናል፥ በደላችንም እንደ ነፋስ ወስዶናል።
ካህኑ ያያል፤ እነሆም፥ በሰውነታቸው ቆዳ ላይ ያለው ቋቁቻ ደብዘዝ ያለ ነጭ ቢሆን በቆዳ ላይ የሚወጣ ሽፍታ ነው፤ ከቆዳው ውስጥ ወጥቶአል፤ እርሱ ንጹሕ ነው።