መክብብ 5:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ደግሞ የሚያሳዝን ክፉ ነገር ነው፥ እንደመጣ እንዲሁ ይሄዳል፥ ድካሙም ለነፋስ ከሆነ ጥቅሙ ምንድነው? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰው ከእናቱ ማሕፀን ዕራቍቱን ይወለዳል፤ እንደ መጣው እንዲሁ ይመለሳል። ከለፋበትም ነገር፣ አንድም እንኳ በእጁ ይዞ ሊሄድ አይችልም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰው ሁሉ ራቁቱን እንደ ተወለደ ባዶ እጁን ተመልሶ ይሄዳል፤ የቱንም ያኽል በሥራ ቢደክም ይዞት የሚሄደው ነገር የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእናቱ ሆድ ራቁቱን እንደ ወጣ እንዲሁ እንደ መጣው ይመለሳል፤ ከጥረቱም በእጁ ሊወስድ የሚችለው ምንም የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእናቱ ሆድ ራቁቱን እንደ ወጣ እንዲሁ እንደ መጣው ይመለሳል፥ ከጥረቱም በእጁ ሊወስድ የሚችለውን ምንም አያገኝም። |
ኤፍሬም ነፋስን ያሰማራል፥ ቀኑን ሙሉ የምሥራቅን ነፋስ ይከተላል፤ ሐሰትንና ዓመጻን ያበዛል፤ ከአሦር ጋር ቃል ኪዳን ያደርጋሉ፥ ወደ ግብጽም ዘይት ይወስዳሉ።