ዘዳግም 8:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጌታ የአምላካችሁን ቃል ስላልሰማችሁ፥ ጌታ ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ ሁሉ እንዲሁ እናንተም ትጠፋላችሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ከፊታችሁ ያሉትን አሕዛብ እንዳጠፋቸው ሁሉ፣ ለአምላካችሁ ለእግዚአብሔር ባለመታዘዛችሁ እናንተም ትጠፋላችሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ባትታዘዝ ወደ ፊት በሄድህ መጠን ከፊትህ የሚገኙትን ሕዝቦች ሁሉ እንደሚደመስስ አንተንም ነቃቅሎ ያጠፋሃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስለ አልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፊታችሁ እንደሚአጠፋቸው እንደ አሕዛብ ሁሉ እናንተም እንዲሁ ትጠፋላችሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስላልሰማችሁ እግዚአብሔር ከፊታችሁ እንደሚያጠፋቸው እንደ አሕዛብ እንዲሁ እናንተ ትጠፋላችሁ። |
ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ለምስክርነት እጠራለሁ፥ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረጅም ዘመን አትኖሩባትም።