ዘዳግም 8:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ዛሬ እኔ አንተን የማዘውን ትእዛዞቹንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ፥ ጌታ አምላክህን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዛሬዪቱ ዕለት የምሰጥህን ትእዛዙን፣ ሕጉንና ሥርዐቱን ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳው ተጠንቀቅ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “እግዚአብሔር አምላክህን በመርሳት፥ እኔ ዛሬ የማዝህን ትእዛዞች፥ ደንቦችና ሥርዓቶች እንዳታፈርስ ተጠንቀቅ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን፥ ሥርዐቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዛሬ እኔ አንተን የማዝዘውን ትእዛዙንና ፍርዱን ሥርዓቱንም ባለመጠበቅ አምላክህን እግዚአብሔርን እንዳትረሳ ተጠንቀቅ፤ |
ሰማያትን የዘረጋውን ምድርንም የመሠረተውን ፈጣሪህን ጌታን ረስተሃል፤ ያጠፋ ዘንድ ባዘጋጀ ጊዜ ከአስጨናቂው ቁጣ የተነሣ ሁልጊዜ ቀኑን ሁሉ ፈርተሃል፤ የአስጨናቂው ቁጣ የት አለ? ምርኮኛው ፈጥኖ ይፈታል፤
ዘርፉንም በልብሳችሁ ላይ አኑሩት እርሱንም በተመለከታችሁ ጊዜ የጌታን ትእዛዝ ሁሉ ታስታውሳላችሁ ታደርጉታላችሁም፥ ምኞታችሁንም በመከተል ያመነዘራችሁባትን የልባችሁንና የዐይኖቻችሁን ፈቃድ የማትከተሉ ትሆናላችሁ።
“አሁንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው በሕይወትም እንድትኖሩ፥ የአባቶቻችሁም አምላክ ጌታ ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ የማስተምራችሁን ሥርዓትና ሕግጋት ስሙ።
“ብቻ አስተውል፥ ነፍስህንም በትጋት ጠብቅ፤ ዐይኖችህ ያዩትን ነገር እንዳትረሳ፥ በሕይወትህም ዘመን ሁሉ ከልብህ እንዳይለይ፥ ለልጆችህም ለልጅ ልጆችህም አሳውቃቸው።
ያልሞላሃቸውንም ሀብትን የሞሉ ቤቶች፥ ያልቆፈርካቸውም የተቆፈሩ ጉድጓዶች፥ ያልተከልሃቸውንም የወይን ተክልና የወይራ ዛፎች፥ ስትበላና ስትጠግብ፥