La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 7:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፥ የምታውቀውንም ክፉውን የግብጽ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በሚጠሉህ ሁሉ ላይ ግን ያመጣባቸዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እግዚአብሔር ከማናቸውም በሽታ ነጻ ያደርግሃል፤ በግብጽ የምታውቃቸውን እነዚያን አሠቃቂ በሽታዎች በሚጠሉህ ሁሉ ላይ እንጂ በአንተ ላይ አያመጣብህም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር ከበሽታ ሁሉ ይጠብቅሃል፤ በግብጽ አገር በነበርክ ጊዜ ካየኸው አሠቃቂ በሽታ ሁሉ ማንኛውንም በአንተ ላይ አያመጣም፤ ነገር ግን እነዚህን በሽታዎች በሚጠሉህ ላይ ያመጣባቸዋል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በግ​ብ​ፃ​ው​ያን ላይ ሲመጣ ያየ​ኸ​ውን ክፉ ሕማ​ምና ደዌ ሁሉ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ንተ ያር​ቅ​ል​ሃል፤ ያየ​ኸ​ው​ንም መከራ ሁሉ ወደ አንተ አያ​መ​ጣ​ውም፤ ከአ​ን​ተም በሚ​ጠ​ሉህ ሁሉ ላይ ይመ​ል​ሰ​ዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እግዚአብሔርም ሕማምን ሁሉ ከአንተ ያርቃል፤ የምታውቀውንም ክፉውን የግብፅ በሽታ ሁሉ በአንተ ላይ አያደርስብህም፥ በጠላቶችህም ሁሉ ላይ ያመጣባቸዋል።

Ver Capítulo



ዘዳግም 7:15
9 Referencias Cruzadas  

ክፉ ነገር ወደ አንተ አይቀርብም፥ መቅሠፍትም ወደ ቤትህ አይገባም።


እርሱም፦ “አንተ የጌታ አምላክህን ቃል ብትሰማ፥ በፊቱም ትክክል የሆነውን ብታደርግ፥ ትእዛዙንም ብታደምጥ፥ ሥርዓቱንም ሁሉ ብትጠብቅ፥ በግብፃውያን ላይ ያመጣሁትን በሽታ አላመጣብህም፤ ፈዋሽህ እኔ ጌታ ነኝና” አለ።


ጌታ አምላካችሁን ታገለግላላችሁ፤ እርሱም እህልህንና ውኃህን ይባርካል፤ በሽታንም ከመካከልህ አርቃለሁ።


ብጉንጅ በጠንቋዮቹና በግብጻውያን ሁሉ ላይ ነበር፤ ጠንቋዮቹም ብጉንጅ ስለ ነበረባቸው በሙሴ ፊት መቆም አልቻሉም፤


በማትድንበት በግብጽ ብጉንጅ፥ በእባጭ፥ በሚመግል ቁስልና በዕከክ ጌታ ያሠቃይሃል።


ደግሞም የምትፈራውን የግብጽ በሽታ ሁሉ ያመጣብሃል፤ በአንተም ላይ ይጣበቃሉ።


ጌታ አምላክህም ይህን ርግማን ሁሉ በጠላቶችህና በሚጠሉህ በሚያሳድዱህም ላይ ያደርገዋል።