ዘዳግም 5:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ስድስት ቀን ሥራ፥ ሥራህንም ሁሉ አከናውን፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድስት ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አከናውን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥራህን ሁሉ በስድስት ቀኖች ሠርተህ ታከናውናለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስድስት ቀን ሥራ፤ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስድስት ቀን ሥራ ተግባርህንም ሁሉ አድርግ፥ |
“ስድስት ቀን ሥራ ይሠራል፤ በሰባተኛው ቀን ግን የዕረፍት ሰንበት ነው፤ የተቀደሰ ጉባኤ ይደረግበታል፤ ምንም ሥራ አትሠሩም፤ በምትኖሩበት ሁሉ ለጌታ ሰንበት ነው።
ሰባተኛው ቀን ግን ለጌታ አምላካችሁ ሰንበት ነው፥ አንተ ወንድ ልጅህም ሴት ልጅህም አገልጋይህም፥ አገልጋይትህም፥ በሬህም፥ አህያህም፥ ከብትህም ሁሉ፥ ወይም በደጆችህም ውስጥ ያለ እንግዳ፥ በእርሱ ምንም ሥራ አትሥሩ፥ አንተ እንደምታርፍ ሁሉ አገልጋይህና አገልጋይትህ እንዲያርፉ።