በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጥመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከመሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ በለሱንም ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፥ ገበያ ባደረጉበትም ቀን አስመሰከርሁባቸው።
ዘዳግም 5:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ ‘ጌታ አምላክህ እንዳዘዘህ፥ እንድትቀድሰው፥ የሰንበትን ቀን ጠብቅ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር ባዘዘህ መሠረት የሰንበትን ቀን ቅዱስ አድርገህ አክብረው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “ ‘እኔ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዝኩህ የሰንበትን ቀን ጠብቅ፤ ቀድሰውም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ዕለተ ሰንበትን ጠብቅ፤ እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህም ቀድሳት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔር አምላክህ እንዳዘዘህ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ ጠብቅ። |
በዚያም ወራት በይሁዳ በሰንበት ቀን የወይን መጥመቂያን የሚረግጡትን፥ ነዶም የሚከመሩትን፥ የወይኑን ጠጅና የወይኑን ዘለላ በለሱንም ልዩ ልዩም ዓይነት ሸክም በአህዮች ላይ የሚጭኑትን፥ በሰንበትም ቀን ወደ ኢየሩሳሌም የሚያስገቡትን አየሁ፥ ገበያ ባደረጉበትም ቀን አስመሰከርሁባቸው።
እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “ጌታ የተናገረው ይህ ነው፦ ነገ የዕረፍት ሰንበት ነው፥ ለጌታ የተቀደሰ ሰንበት ነው፤ የምትጋግሩትን ጋግሩ፥ የምትቀቅሉትንም ቀቅሉ፥ የተረፈውን ሁሉ ተውት ለጥዋት ለእናንተ አስቀምጡት።”
“አንተ ግን ለእስራኤል ልጆች እንዲህ ብለህ ንገራቸው፦ ‘ሰንበቶቼን ፈጽሞ ጠብቁ፥ ይህ የምቀድሳችሁ ጌታ እኔ እንደሆንሁ እንድታውቁ በእኔና በእናንተ መካከል ለትውልዶቻችሁ ምልክት ነውና።
ያገለግሉት ዘንድ የጌታንም ስም ለመውደድ አገልጋዮቹም ለመሆን ወደ ጌታ የሚጠጉትንም መጻተኞች፥ እንዳያረክሱት ሰንበትን የሚጠብቁትን፥ በቃል ኪዳኔኔም የሚጸኑትን ሁሉ፥
ፈቃድህን በተቀደሰው ቀኔ ከማድረግ፥ እግርህን ወደ ሰንበት፥ ሰንበትንም ደስታ፥ ጌታንም የቀደሰውን ክቡር ብትለው፥ በራስህ መንገድህን ከመጓዝ፥ ፈቅድህንም ከመፈጸም፥ ከንቱ ነገርንም ከመናገር ተከልክለህ ብታከብረው፥