ዘዳግም 34:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ፊት ለፊት ያወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል አልተነሣም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ፊት ለፊት ያነጋገረው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ በእስራኤል ከቶ ተነሥቶ አያውቅም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔር ፊት ለፊት እንደ ተናገረው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርን ፊት ለፊት እንዳወቀው እንደ ሙሴ ያለ ነቢይ ከዚያ ወዲህ በእስራኤል ዘንድ አልተነሣም፤ |
ሰው ከባልንጀራው ጋር እንደሚነጋገር ጌታም ከሙሴ ጋር ፊት ለፊት ይነጋገር ነበር። ሙሴ ወደ ሰፈሩ ሲመለስ አገልጋዩ የሆነው ወጣቱ የነዌ ልጅ ኢያሱ ግን ከድንኳኑ አይለይም ነበር።
እንዲሁም አደረጉ፤ አሮንም እጁን ዘረጋ፥ በበትሩም የምድሩን ትቢያ መታ፥ በሰውና በእንስሳም ላይ ተናካሽ ትንኝ ሆነ፤ በግብጽ ምድር ያለ የምድር ትቢያ ሁሉ ተናካሽ ትንኝ ሆነ።