ዘዳግም 33:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእርግጥ ሕዝቡን ይወዳል፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጁ ናቸው፤ እነርሱም በእግሮችህ ሥር ይሰግዳሉ፤ መመሪያህንም ከአንተ ይቀበላሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በርግጥ ሕዝቡን የምትወድድ አንተ ነህ፤ ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ውስጥ ናቸው። ከእግርህ ሥር ሁሉ ይሰግዳሉ፤ ከአንተ ትእዛዝ ይቀበላሉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር በእውነት ሕዝቡን ይወዳል፤ ቅዱሳኑን ሁሉ ይጠብቃል፤ እነርሱም በእግሩ ሥር ተንበርክከው ይሰግዳሉ፤ መመሪያውንም ይቀበላሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሕዝቡም ራራላቸው፤ ቅዱሳን ሁሉ ከእጅህ በታች ናቸው፤ እነርሱም የአንተ ናቸው። ቃሎችህንም ይቀበላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሕዝቡንም ወደዳቸው፤ 2 ቅዱሳኑ ሁሉ በእጅህ ናቸው፤ 2 በእግሮችህም አጠገብ ተቀመጡ፤ 2 ቃሎችህን ይቀበላሉ። |
ጻድቃንና ጠቢባን፥ ሥራዎቻቸውም በእግዚአብሔር እጅ እንደ ሆኑ፥ ይህን ሁሉ እመረምር ዘንድ በልቤ አኖርሁ፥ ፍቅርም ሆነ ጥል ቢሆን ሰው አያውቅም፤ ሁሉም በፊታቸው ነው።
“ሂድ፥ በኢየሩሳሌም ጆሮዎች ላይ አውጅ፥ እንዲህም በል፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ የብላቴንነትሽን ጽኑ ፍቅር የታጨሽበትንም ፍቅር፥ በምድረ በዳ ዘር ባልተዘራበት ምድር እንደ ተከተልሽኝ አስታውሼዋለሁ።
ለእነርሱም ከማደርገው በጎነት አልመለስም ስል፥ ከእነርሱ ጋር የዘለዓለምን ቃል ኪዳን አደርጋለሁ፤ ከእኔም ዘንድ ፈቀቅ እንዳይሉ መፈራቴን በልባቸው ውስጥ አኖራለሁ።
ወድጃችኋለሁ ይላል ጌታ፤ እናንተ ግን፦ “እንዴት ወደድከን?” ትላላችሁ። ዔሳው የያዕቆብ ወንድም አልነበረምን? ይላል ጌታ። ሆኖም ያዕቆብን ወደድኩት።
ሰዎቹም የሆነውን ነገር ለማየት ወጥተው ወደ ኢየሱስ መጡ፤ አጋንንትም የወጡለትን ሰው ለብሶ፥ ልቡም ተመልሶ፥ በኢየሱስ እግር አጠገብ ተቀምጦ አገኙትና ፈሩ።
“እኔ የኪልቅያ በምትሆን በጠርሴስ የተወለድሁ፥ በዚችም ከተማ በገማልያል እግር አጠገብ ያደግሁ፥ የአባቶችንም ሕግ ጠንቅቄ የተማርሁ፥ ዛሬውንም እናንተ ሁሉ እንድትሆኑ ለእግዚአብሔር ቀናተኛ የሆንሁ አይሁዳዊ ሰው ነኝ።
ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለጌታ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ ለራሱ የተለየ ሕዝብ እንድትሆንለት ጌታ በምድር ላይ ከሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ አንተን መርጦሃል።