ዘዳግም 33:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ ሆይ፥ ሀብቱን ባርክ፥ የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ የጠላቱን አከርካሪ ስበር፤ የሚጠሉትም ዳግመኛ አይነሡ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀይሉን ሁሉ ባርክለት፤ በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤ በርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቍረጠው፤ ጠላቶቹንም እንዳያንሠራሩ አድርገህ ምታቸው።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ሀብታቸውን ባርክ፤ የእጃቸውን ሥራ ተቀበል፤ የጠላቶቻቸውን ኀይል አድክም፤ የሚጠሉአቸውም ዳግመኛ እንዳያንሰራሩ አድርግ!” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ ኀይሉን ባርክ፤ የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ በሚቃወሙት ጠላቶቹ ላይ መከራን አውርድ፤ የሚጠሉትም አይነሡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አቤቱ፥ ሀብቱን ባርክ፥ 2 የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ 2 የሚነሣበትን ወገብ ውጋው፥ 2 የሚጠሉትም አይነሡ። |
እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።
ቀኖቹንም በፈጸሙ ጊዜ በስምንተኛው ቀንና ከዚያም በኋላ፥ ካህናቱ የሚቃጠል መሥዋዕታችሁንና የሰላም መሥዋዕታችሁን በመሠዊያው ላይ ያደርጋሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።