Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ዘዳግም 33:11 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 አምላክ ሆይ! ሀብታቸውን ባርክ፤ የእጃቸውን ሥራ ተቀበል፤ የጠላቶቻቸውን ኀይል አድክም፤ የሚጠሉአቸውም ዳግመኛ እንዳያንሰራሩ አድርግ!”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እግዚአብሔር ሆይ፤ ኀይሉን ሁሉ ባርክለት፤ በእጁ ሥራ ደስ ይበልህ፤ በርሱ ላይ የሚነሡበትን ሽንጣቸውን ቍረጠው፤ ጠላቶቹንም እንዳያንሠራሩ አድርገህ ምታቸው።”

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ጌታ ሆይ፥ ሀብቱን ባርክ፥ የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ የጠላቱን አከርካሪ ስበር፤ የሚጠሉትም ዳግመኛ አይነሡ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 አቤቱ ኀይ​ሉን ባርክ፤ የእ​ጁ​ንም ሥራ ተቀ​በል፤ በሚ​ቃ​ወ​ሙት ጠላ​ቶቹ ላይ መከ​ራን አው​ርድ፤ የሚ​ጠ​ሉ​ትም አይ​ነሡ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 አቤቱ፥ ሀብቱን ባርክ፥ 2 የእጁንም ሥራ ተቀበል፤ 2 የሚነሣበትን ወገብ ውጋው፥ 2 የሚጠሉትም አይነሡ።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 33:11
18 Referencias Cruzadas  

ኦርናም “ይህን ሁሉ ለንጉሡ ሰጥቶ እግዚአብሔር መሥዋዕትህን ይቀበልልህ” አለው።


መባህን ሁሉ ይቀበልልህ፤ በመሥዋዕትህም ደስ ይበለው።


ሰውን በነገር ወንጀለኛ የሚያደርጉ፥ ተከሳሽንም በፍርድ ሸንጎ የሚያጠምዱ፥ በሐሰተኛ ምስክር ንጹሕ ሰው ፍትሕ እንዳያገኝ በሐሰት የሚመሰክሩትን ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል።


እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምን ወለድሽኝ? ዕድል ፈንታዬ ከአገሪቱ ሕዝብ ሁሉ ጋር መከራከርና መነታረክ ሆኗል፤ እኔ ገንዘብ ለማንም አላበደርኩም ወይም ከማንም አልተበደርኩም፤ ሆኖም ሰው ሁሉ ይረግመኛል።


እግዚአብሔር ሆይ! በሚያሳድዱኝ ሁሉ ላይ ኀፍረትን አምጣባቸው፤ እኔን ግን አታሳፍረኝ፤ እነርሱ እንዲሸበሩ አድርግ፤ እኔን ግን አታስደንግጠኝ፤ ተሰባብረው እስኪደቁ ድረስ ደጋግመህ አጥፋቸው።


እነዚህ ቀኖች ካለፉ በኋላ ከስምንተኛው ቀን ጀምሮ ካህናቱ የሚቃጠልና የደኅንነት መሥዋዕታችሁን ያቀርባሉ፤ እኔም እቀበላችኋለሁ፤” ይላል ልዑል እግዚአብሔር።


እናንተ በፍርድ አደባባይ የሚገሥጻችሁን ጠላችሁ፤ እውነት የሚናገረውንም ተጸየፋችሁ።


እንደገናም ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን፦ “እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተን የማይቀበል እኔን አይቀበልም፤ እኔን የማይቀበልም የላከኝን አይቀበልም፤” አላቸው።


ሥርዓትህን ለያዕቆብ፥ ሕግህንም ለእስራኤል ያስተምራሉ፤ በፊትህ ዕጣን ያጥናሉ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትም በመሠዊያህ ላይ ያቀርባሉ።


ስለ ብንያምም ነገድ እንዲህ አለ፦ “እግዚአብሔር የሚወደው ያለ ስጋት ይረፍ፤ ኀያሉ አምላክ ቀኑን ይጠብቀዋል። በእግዚአብሔር ጥበቃም ሥር ይኖራል።”


ስለዚህ ይህን ምክር የሚቃወም፥ የሚቃወመው ቅዱስ መንፈሱን የሚሰጣችሁን እግዚአብሔርን እንጂ ሰውን አይደለም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos