ዘዳግም 3:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዚያን ጊዜ ለጌታ እኔ እንዲህ ብዬ ለመንሁ፦ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያ ጊዜ እግዚአብሔርን እንዲህ ብዬ ለመንሁት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በዚያን ጊዜ እንዲህ ስል አጥብቄ ጸለይኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በዚያም ዘመን እኔ እግዚአብሔርን እንዲህ ብዬ ለመንሁት፦ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ዘመን እኔ ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ብዬ ለመንሁ፦ |
‘ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህን የጸናችውንም እጅህን ለእኔ ለአገልጋይህ ማሳየት ጀምረሃል፥ በሰማይም ሆነ በምድርም እነዚህ ሥራዎችና ኃያል ተግባራት እንደ አንተ ማድረግ የሚችል አምላክ ማን ነው?