ዘዳግም 3:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ‘ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህን የጸናችውንም እጅህን ለእኔ ለአገልጋይህ ማሳየት ጀምረሃል፥ በሰማይም ሆነ በምድርም እነዚህ ሥራዎችና ኃያል ተግባራት እንደ አንተ ማድረግ የሚችል አምላክ ማን ነው? Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም24 “ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፤ ታላቅነትህንና ብርቱ ክንድህን ለእኔ ለባሪያህ እነሆ ማሳየት ጀምረሃል፤ ለመሆኑ በሰማይም ሆነ በምድር፣ አንተ የምታደርጋቸውን ሥራዎችና ታላላቅ ድርጊቶች መፈጸም የሚችል አምላክ ማነው? Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ‘ልዑል እግዚአብሔር ሆይ! ወደ ፊት ከምታደርጋቸው ታላላቅና አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ያሳየኸኝ የመጀመሪያውን ክፍል ብቻ እንደ ሆነ ዐውቃለሁ፤ አንተ የምታደርጋቸውን ታላላቅ ነገሮች የሚያደርግ ሌላ አምላክ በሰማይም ሆነ በምድር የለም። Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ! ታላቅነትህንና ኀይልህን፥ የጸናች እጅህንና የተዘረጋች ክንድህን ለእኔ ለአገልጋይህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይና በምድርም እንደ ሥራህ፥ እንደ ኀይልህም ይሠራ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው? Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ጌታ እግዚአብሔር ሆይ፥ ታላቅነትህን የጸናችውንም እጅህን ለእኔ ለባሪያህ ማሳየት ጀምረሃል፤ በሰማይና በምድርም እንደ ሥራህ እንደ ኃይልህም ይሠራ ዘንድ የሚችል አምላክ ማን ነው? Ver Capítulo |