“በከተማ ትባረካለህ፥ በዕርሻህም ትባረካለህ።
በከተማ ትባረካለህ፣ በዕርሻህም ትባረካለህ።
“እግዚአብሔር ከተሞችህንና እርሻዎችህን ይባርካል።
አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ፤ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ።
አንተ በከተማ ቡሩክ ትሆናለህ፥ በእርሻም ቡሩክ ትሆናለህ።
ይስሐቅም በዚያች ምድር ዘርን ዘራ፥ በዚያች ዓመትም መቶ እጥፍ አገኘ፥ እግዚአብሔርም ባረከው።
ዮሴፍ በጲጥፋራ ቤትና ባለው ሀብት ሁሉ ላይ ከተሾመበት ጊዜ ጀምሮ ጌታ የግብፃዊውን ቤት ባረከ፥ የጌታም በረከት በግቢም በውጭም ባለው የጲጥፋራ ሀብት ንብረት ሁሉ ላይ ሆነ።
ንጉሡም የሕጉን ቃላት በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ።
ሃሌ ሉያ። ጌታን የሚፈራ፥ ትእዛዙንም እጅግ የሚወድድ ሰው ብፁዕ ነው።
ዘር በጎተራ አሁንም አለን? ወይንና የበለስ ዛፍ ሮማንና የወይራ ዛፍ አላፈሩም፤ ከዚህች ቀን ጀምሬ እባርካችኋለሁ።
ጌታ ይባርክህ፥ ይጠብቅህም፤
“በከተማ ትረገማለህ፤ በዕርሻም ትረገማለህ።
“የማሕፀንህ ፍሬ፥ የምድርህ አዝመራ፥ የእንስሳትህ ግልገሎች፥ የከብትህ ጥጃ፥ የበግና የፍየል ግልገሎችህም ይባረካሉ።