ዘዳግም 27:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታ እግዚአብሔርን ታዘዝ፤ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቅ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህን እግዚአብሔርን ታዘዝ፤ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዐቱን ጠብቅ።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህም ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዞችና ድንጋጌዎች ሁሉ በመጠበቅ ለእኔ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር ቃል ታዛዥ ሁን።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የአምላክህንም የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ ዛሬም የማዝዝህን ትእዛዙንና ሥርዐቱን አድርግ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለአምላክህም ለእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ፥ ዛሬም የማዝዝህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን አድርግ። |
ሰው ሆይ፥ መልካም ምን እንደሆነ ለአንተ ነግሮሃል፤ ፍትሕን እንድታደርግ፥ ምሕረትን እንድትወድና ከአምላክህም ጋር በትሕትና እንድትሄድ ካልሆነ በቀር ጌታ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው?
ሙሴና ሌዋውያን ካህናትም ለእስራኤል ሁሉ እንዲህ አሉ፦ “እስራኤል ሆይ፥ ዝም ብለህ አድምጥ! አንተ ዛሬ የጌታ እግዚአብሔር ሕዝብ ሆነሃል።