Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ዘዳግም 26:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ጌታ አምላክህ እንደሆነ በመንገዱም እንደምትሄድ፥ ሥርዓቱን፥ ትእዛዙንና ሕጉን እንደ ምትጠብቅና እንደምትታዘዝለት ተናግረሃል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 እግዚአብሔር አምላክህ እንደ ሆነ በመንገዱም እንደምትሄድ፣ ሥርዐቱን፣ ትእዛዙንና ሕጉን እንደምትጠብቅና እንደምትታዘዝለት በዛሬዪቱ ዕለት ተናግረሃል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 እግዚአብሔር አምላክህ መሆኑንና በሕጉም የምትመራ መሆንህን ዛሬ አንተ አረጋግጠሃል፤ ሥርዓቱን፥ ትእዛዞቹንና ሕጎቹን ለመጠበቅና ታዛዥ ለመሆን ቃል ገብተሃል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 አን​ተም በመ​ን​ገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን፥ ፍር​ዱ​ንም ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ቃሉ​ንም ትሰማ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላ​ክህ እን​ዲ​ሆን ዛሬ መር​ጠ​ሃል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 አንተ በመንገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ሥርዓቱንና ትእዛዙን ፍርዱንም ትጠብቅ ዘንድ፥ ቃሉንም ትሰማ ዘንድ እግዚአብሔር እርሱ አምላክህ መሆኑን ዛሬ አስታውቀሃል።

Ver Capítulo Copiar




ዘዳግም 26:17
26 Referencias Cruzadas  

እነሆ፤ ጌታ መዳኛዬ ነው፤ እታመናለሁ፤ ደግሞም አልፈራም፤ ጌታ እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ የመዳኔ ምክንያትም ሆኖአል።”


የቃል ኪዳኑንም መጽሐፍ ወስዶ በሕዝቡ ጆሮ ላይ አወጀ፤ እነርሱም፦ “ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለንም” አሉ።


አስቀድመው ራሳቸውን ለጌታ ሰጡ፥ ከዚያም በእግዚአብሔር ፈቃድ ለእኛም ሰጡ፥ እንጂ እኛ አስበንበት ያደረግነው አይደለም።


የሰውነታችሁን ክፍሎች የክፋት መሣሪያ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፤ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፤ የሰውነታችሁንም ክፍሎች የጽድቅ መሣሪያ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።


የእርሱ የምሆንና ደግሞ የማመልከው የእግዚአብሔር መልአክ በዚች ሌሊት በአጠገቤ ቆሞ ነበርና፤ እርሱም


ይህ፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ይላል፥ ያም በያዕቆብ ስም ይጠራል፤ ይህም፦ እኔ የእግዚአብሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽፋል፤ በእስራኤልም የቁልምጫ ስም ይጠራል።


ብቻ የጌታ ባርያ ሙሴ አምላካችሁን ጌታን እንድትወድዱ፥ መንገዱንም ሁሉ እንድትሄዱ፥ ትእዛዙንም እንድትጠብቁ፥ እርሱንም በጽኑ እንድትይዙት፥ በፍጹምም ልባችሁ በፍጹምም ነፍሳችሁ እንድታገለግሉት ያዘዛችሁን ትእዛዙንና ሕጉን በጥንቃቄ አድርጉ።”


ጌታ አምላክህን በመውደድ፥ በመንገዱም በመሄድና ትእዛዙን፥ ሥርዓቱንና ሕጉን በመጠበቅ ያዘዝሁን ካደርግክ፤ በሕይወት ትኖራለህ፤ ትበዛለህም፤ ጌታ አምላክም ትወርሳት ዘንድ በምትገባበት ምድር ይባርክሃል።


ይህ የሚሆነውም ለጌታ ለእግዚአብሔር ፈጽመህ ስትታዘዝና ዛሬ የምሰጥህን እነዚህን ትእዛዞች ሁሉ ብትጠነቀቅ ነው።


ይህም የሚሆነው፥ ዛሬ እኔ የማዝዝህን ትእዛዝ ሁሉ ከጠበቅህ፥ በጌታ በአምላክህ ፊት ትክክል የሆነውን ካደረግህ፥ የጌታ የአምላክህን ቃል ከሰማህ ነው።”


ሙሴንም እንዲህ አሉት፦ “አንተ ተናገረን እኛም እንሰማለን፤ ነገር ግን እንዳንሞት እግዚአብሔር አይናገረን።”


አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።


ንጉሡም በስፍራው ቆሞ ጌታን ተከትሎ እንዲሄድ፥ ትእዛዛቱንና ምስክሩን ሥርዓቱንም በፍጹም ልቡና በፍጹም ነፍሱ እንዲጠብቅ፥ በዚህም መጽሐፍ የተጻፈውን የቃል ኪዳን ቃል እንዲያደርግ በጌታ ፊት ቃል ኪዳን አደረገ።


ጌታ ኃይሌና መዝሙሬ ነው፥ መድኃኒቴም ሆነልኝ፤ ይህ አምላኬ ነው አመሰግነዋለሁም፥ የአባቴ አምላክ ከፍ ከፍ አደርገዋለሁ።


ወደ አባቴ ቤትም በጤና ብመለስ፥ እግዚአብሔር አምላኬ ይሆንልኛል፥


ሕዝቡም ሁሉ በአንድነት ሆነው፦ “ጌታ ያለውን ሁሉ እናደርጋለን” ብለው መለሱ፤ ሙሴም የሕዝቡን ቃል ወደ ጌታ አደረሰ።


በብርታትዋ ልባችሁን አኑሩ፥ ቅጥሮችዋን መርምሩ፥ ለሚመጣው ትውልድ ትነግሩ ዘንድ።


ጌታ እግዚአብሔርን ታዘዝ፤ ዛሬ የምሰጥህን ትእዛዙንና ሥርዓቱን ጠብቅ።”


እዚህ የቆምኸው ጌታ ዛሬ ከአንተ ጋር ወደሚያደርገውና በመሓላ ወደሚያጸናው ኪዳን ከጌታህ ከእግዚአብሔር ጋር ትገባ ዘንድ፥


ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ አላቸው፦ “እንድታገለግሉት እናንተ ጌታን እንደ መረጣችሁ በራሳችሁ ላይ ምስክሮች ናችሁ፤” እነርሱም፦ “ምስክሮች ነን” አሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios