ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደውባቸው ነበር፥ ምግብ፥ ወይና አርባ ሰቅል ብር ከእነሱ ይወስዱ ነበር፤ አገልጋዮቻቸው ደግሞ ሕዝቡን ይጨቁኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።
ዘዳግም 25:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደክመህና ዝለህ በነበርህበት ጊዜ፥ በጉዞ ላይ አግኝተውህ፥ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአብሔርንም አልፈሩም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደክመህና ዝለህ በነበርህበት ጊዜ፣ በጕዞ ላይ አግኝተውህ፣ ከኋላ ያዘግሙ የነበሩትን ሁሉ ገደሉ፤ እግዚአብሔርንም አልፈሩም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ እግዚአብሔርን የሚፈሩ አይደሉም፤ አንተ በጒዞ ላይ ደክሞህ በነበረ ጊዜ በኋላ በኩል አደጋ ጣሉብህ፤ ደክመው ወደ ኋላ ያዘግሙ የነበሩትንም ሁሉ ገደሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በመንገድ ላይ እንደ ተቃወመህ፥ አንተም ተርበህና ደክመህ ሳለህ ጓዝህንና ከአንተ በኋላ ደክመው የነበሩትን ሁሉ እንደ መታ፤ እግዚአብሔርንም አልፈራውም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በመንገድ ላይ እንደ ተቃወመህ፥ አንተም ተስኖህ ደክመህም ሳለህ ከአንተ በኋላ ደክመው የነበሩትን ሁሉ እንደ መታ፤ እግዚአብሔርንም አልፈራም። |
ከእኔ በፊት የነበሩት የቀድሞ ገዢዎች ግን በሕዝቡ ላይ አክብደውባቸው ነበር፥ ምግብ፥ ወይና አርባ ሰቅል ብር ከእነሱ ይወስዱ ነበር፤ አገልጋዮቻቸው ደግሞ ሕዝቡን ይጨቁኑአቸው ነበር፤ እኔ ግን እግዚአብሔርን ስለ ፈራሁ እንዲህ አላደረግሁም።