ዘዳግም 19:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁለቱም ወገኖች በጌታ ፊት፥ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ክርክሩ የሚመለከታቸው ሁለቱ ሰዎች በእግዚአብሔር ፊት፣ በዚያ ወቅት በሚያገለግሉት ካህናትና ፈራጆች ፊት ይቁሙ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁለቱም ወገኖች እግዚአብሔር በሚመለክበት ቦታ ወደሚገኙት የወቅቱ ካህናትና ዳኞች ወደሆኑት ፊት ይቅረቡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁለቱ ጠበኞች በእግዚአብሔር ፊት በካህናቱና በዚያ ዘመን በሚፈርዱ ፈራጆች ፊት ይቆማሉ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁለቱ ጠበኞች በእግዚአብሔር ፊት በካህናቱና በዚያ ዘመን በሚፈርዱ ፈራጆች ፊት ይቆማሉ፤ |
ሰዎች ስለ በሬ ወይም ስለ አህያ ወይም ስለ በግ ወይም ስለ ልብስ ወይም ስለ ሌላ ስለ ጠፋ ነገር ቢካሰሱ፥ አንዱም፦ ይህ የእኔ ነው ቢል ክርክራቸው ወደ እግዚአብሔር ይምጣ፤ እግዚአብሔርም የፈረደበት እርሱ ለባልንጀራው እጥፍ አድርጎ ይክፈል።
እንዲያገለግሉና በጌታ ስም እንዲባርኩ፥ በማንኛውም የክርክርና የጥቃት ጉዳዮች ሁሉ ላይ ውሳኔ እንዲሰጡ፥ አምላክህ ጌታ መርጦአቸዋልና የሌዊ ልጆች ካህናቱ ወደ ፊት ይቅረቡ።