ዘዳግም 18:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ ከገዛ ወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱን አድምጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር እንደ እኔ ያለ ነቢይ ከወንድሞቻችሁ መካከል ያስነሣልሃል፤ እርሱን ስማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ከወገኖቻችሁ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ መርጦ ያስነሣላችኋል፤ እርሱ የሚላችሁንም ሁሉ በመስማት ታዛዦች ሁኑ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ስሙት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህን እግዚአብሔርን በኮሬብ ስብሰባ ተደርጎ በነበረበት ቀን፦ እንዳልሞት የአምላኬን የእግዚአብሔር ድምፅ ደግሞ አልስማ፥ ይህችን ታላቅ እሳት ደግሞ አልይ ብለህ እንደ ለመንኸው ሁሉ፥ አምላክህ እግዚአብሔር ከአንተ መካከል ከወንድሞችህ እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሣልሃል፤ እርሱንም ታደምጣለህ። |
እኔ በምሳሌ ሳይሆን እፊት ለፊት ከእርሱ ጋር በግልጥ እነጋገራለሁ፤ የጌታንም ሀልዎተ-ቅርፅ ይመለከታል፤ ታዲያ፥ በባርያዬ በሙሴ ላይ ለመናገር ለምን አልፈራችሁም?”
እርሱም ገና እየተናገረ ሳለ እነሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፤ እነሆ ከደመናው ውስጥ “በእርሱ ደስ የሚለኝ የተወደደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት” የሚል ድምፅ መጣ።
እነሆም፥ በኢየሩሳሌም ስምዖን የሚባል አንድ ሰው ነበረ፤ ይህም ሰው የእስራኤልን መጽናናት የሚጠብቅ፥ ጻድቅና ትጉህም ነበረ፤ መንፈስ ቅዱስም በእርሱ ላይ ነበረ።
እርሱም “ምንድነው?” አላቸው። እነርሱም እንዲህ አሉት፦ “በእግዚአብሔርና በሕዝቡ ሁሉ ፊት በሥራና በቃል ብርቱ ነቢይ ስለ ነበረው ስለ ናዝሬቱ ስለ ኢየሱስ ነው፤
ሁሉንም ፍርሃት ያዛቸው፤ እግዚአብሔርንም እንዲህ እያሉ አመሰገኑ፦ “ታላቅ ነቢይ በእኛ መካከል ተነሥቶአል!” “እግዚአብሔርም ሕዝቡን ጐብኝቶአል!”
እናንተ በእሳቱ ምክንያት ፈርታችሁ፥ ወደ ተራራውም አልወጣችሁምና፤ በዚያን ጊዜ፥ እኔ የጌታን ቃል ልነግራችሁ፥ በጌታና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦