ዘዳግም 15:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደሙን ግን እንደ ውሃ መሬት ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደማቸውን እንደ ምግብ አድርጋችሁ አትመገቡት፤ ነገር ግን ደሙን እንደ ውሃ በምድር ላይ አፍስሱት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ደሙን በምድር ላይ እንደ ውኃ አፍስሰው እንጂ አትብላው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ደሙን እንደ ውኃ በምድር ላይ አፍስሰው እንጂ አትብላው። |
ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ከደም ጋር ትበላላችሁ፥ ዓይናችሁንም ወደ ጣዖቶቻችሁ ታነሣላችሁ፥ ደምንም ታፈስሳላችሁ፤ በውኑ ምድሪቱን ትወርሳላችሁን?
“ከእስራኤልም ልጆች ወይም በመካከላቸው ከሚኖር እንግዳ ማናቸውም ሰው ደም ቢበላ፥ ደም በሚበላው በዚያ ሰው ላይ ፊቴን አጠቊርበታለሁ፥ ያንንም ሰው ከሕዝቡ መካከል ለይቼ አጠፋዋለሁ።
“ሆኖም ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ መጠን፥ በየትኛውም ከተማህ፥ እንስሳትህን ሚዳቋም ሆነ ድኩላ ዐርደህ የምትፈልገውን ያህል ሥጋ ብላ። በሥርዓቱ መሠረት ንጹሕ የሆነም ሆነ ያልሆነ ሰው ከዚሁ ሥጋ ሊበላ ይችላል።
ከዚያም ለሳኦል፥ “እነሆ፤ ሕዝቡ ሥጋውን ከነደሙ በመብላት ጌታን እየበደለ ነው” ተብሎ ተነገረው። ሳኦልም፥ “ይህ የክሕደት ተግባር ነው! አንድ ትልቅ ድንጋይ አንከባላችሁ ወደዚህ አምጡልኝ” አለ።