La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘዳግም 15:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

የአገልጋይህን የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፥ አንድ የቅጥር ሠራተኛ ከሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና፤ እርሱን ነጻ ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ። ጌታ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋይህን ዐርነት ማውጣቱ ከባድ መስሎ አይታይህ፤ የስድስት ዓመት አገልግሎቱ፣ አንድ የቅጥር ሠራተኛ የሚሰጠው አገልግሎት ዕጥፍ ነውና። አምላክህ እግዚአብሔር በምታደርገው ነገር ሁሉ ይባርክሃል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እርሱንም ነጻ ባወጣኸው ጊዜ አንድ ተቀጣሪ ለስድስት ዓመት ከሚሰጥህ እጥፍ አገልግሎት ስለ ሰጠህ ቅር አይበልህ። እንግዲህ ይህን አድርግ፤ እግዚአብሔርም በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እር​ሱ​ንም አር​ነት ባወ​ጣ​ኸው ጊዜ የም​ን​ደ​ኝ​ነ​ቱን ሥራ ሁለት ዕጥፍ አድ​ርጎ ስድ​ስት ዓመት አገ​ል​ግ​ሎ​ሃ​ልና አያ​ስ​ጨ​ን​ቅህ፤ አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በም​ት​ሠ​ራው ሁሉ ይባ​ር​ክ​ሃል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እርሱንም አርነት ባወጣኸው ጊዜ የምንደኝነቱን ሥራ ሁለት እጥፍ አድርጎ ስድስት ዓመት አገልግሎሃልና አይክበድህ፤ አምልካህም እግዚአብሔር በምትሠራው ሁሉ ይባርክሃል።

Ver Capítulo



ዘዳግም 15:18
6 Referencias Cruzadas  

አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እንደ ተቀጣሪ ደሞዝተኛ የሞዓብ ክብር፥ ምንም ያህል ሕዝቡ ቢበዛ፥ በሦስት ዓመት ውስጥ ይዋረዳል፤ የሚተርፈውም ሕዝብ እጅግ ጥቂትና ደካማ ይሆናል።”


ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤


ይልቅስ ያለ ቅሬታ በለጋስነት በልግስና ስጠው፤ ከዚህም የተነሣ ጌታ አምላክህ በሥራህ ሁሉና እጅህ ባረፈበት በማናቸውም ነገር ይባርክሃል።


ጆሮውን ከቤትህ መዝጊያ ላይ በማስደገፍ በወስፌ ትበሳዋለህ፤ ከዚያም ዕድሜ ልኩን አገልጋይህ ይሆናል። በሴት አገልጋይህም ላይ እንደዚሁ አድርግ።


“የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋዎችህን ተባዕት በኩር ሁሉ ለጌታ ለእግዚአብሔር ትቀድሳለህ። የበሬህን በኩር አትሥራበት፤ የበግህንም በኩር አትሸልት፤