Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 16:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እንደ ተቀጣሪ ደሞዝተኛ የሞዓብ ክብር፥ ምንም ያህል ሕዝቡ ቢበዛ፥ በሦስት ዓመት ውስጥ ይዋረዳል፤ የሚተርፈውም ሕዝብ እጅግ ጥቂትና ደካማ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “የተቀጠረ ሠራተኛ ቀን እንደሚቈጥር፣ የሞዓብ ክብርና የሕዝቧ ብዛት በሦስት ዓመት ውስጥ ይዋረዳል፤ የሚቀረውም ሕዝብ ጥቂትና ደካማ ይሆናል።”

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 አሁን ግን እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “የአንድ ጊዜያዊ የቅጥር ሠራተኛ የሥራ ጊዜ እንደሚቋረጥ የሞአብ ክብርና ብዙ ሕዝቦችዋ በሦስት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይዋረዳል፤ ከሕዝቧ የተረፉትም በጣም ጥቂቶችና ደካሞች ይሆናሉ።”

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 አሁ​ንም እን​ዲህ እላ​ለሁ፤ በሦ​ስት ዓመት ውስጥ እንደ ምን​ደኛ ዓመት የሞ​ዓብ ክብር ከብዙ ሀብ​ትዋ ጋር ይዋ​ረ​ዳል፤ በቍ​ጥ​ርም ጥቂት ይቀ​ራል፤ ክብ​ር​ዋም አይ​ገ​ኝም።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 አሁን ግን እግዚአብሔር፦ በሦስት ዓመት ውስጥ እንደ ምንደኛ ዓመት የሞዓብ ክብርና የሕዝቡ ሁሉ ብዛት ይዋረዳል፥ ቅሬታውም እጅግ ያነሰና የተጠቃ ይሆናል ይላል።

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 16:14
18 Referencias Cruzadas  

ሞዓብም በጌታ ላይ ኰርቶአልና ከእንግዲህ ወድያ ሕዝብ አይሆንም፥ እርሱም ይጠፋል።


የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊሽር፥ የምድርንም ክብር ሁሉ ሊያስንቅ የሠራዊት ጌታ ይህን ወስኗል።


ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ጠቢብ በጥበቡ አይመካ፥ ኃያልም በኃይሉ አይመካ፥ ባለ ጠጋም በብልጥግናው አይመካ፤


የጌታም እጅ በዚህ ተራራ ላይ ታርፋለች፤ ጭድም በጭቃ ውስጥ እንደሚረገጥ እንዲሁ ሞዓብ በሥፍራው ይረገጣል።


በዚያን ቀን የያዕቆብ ክብር ይደበዝዛል፥ የሰውነቱም ውፍረት ይመነምናል።


ልቤ ስለ ሞዓብ አለቀሰ፤ ከእርሷ የሚሸሹ ወደ ዞዐር ወደ ዔግላት ሺሊሺያ ኮበለሉ፤ በሉሒት አቀበት ላይ እያለቀሱ ወጡ፤ በሖሮናይምም መንገድ የዋይታ ጩኽት አሰሙ።


ነገር ግን ሕፃኑ ክፉውን መተውና መልካሙን መምረጥ ከመቻሉ በፊት የፈራሃቸው የሁለቱ ነገሥታት ምድር ባድማ ይሆናል።


ይልቅስ እጅህን ፍታለት፤ የሚያስፈልገውንም ሁሉ አበድረው።


ያዕቆብም፥ የላባ ልጆች፦ “ያዕቆብ የአባታችን የሆነውን ሁሉ ወሰደ፥ የአባታችን ከነበረውም ይህንም ሁሉ ሀብት አገኘ” ሲሉ ሰማ።


“የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? ቀኖቹ እንደ ምንደኛ ቀኖች አይደሉምን?


እንደ ምንደኛ ዕድሜው እስኪፈጸም ድረስ ያርፍ ዘንድ ከእርሱ ጥቂት ዘወር በል።”


በምዕራብ በኩል በፍልስጥኤም ተረተር ላይ ይወርዳሉ፤ ሁለቱም ተባብረው በምሥራቅ ያለውን ሕዝብ ይዘርፋሉ፤ በኤዶምና በሞዓብ ላይ እጃቸውን ያነሣሉ፤ አሞናውያንም ይገዙላቸዋል።


ጌታ በሞዓብ ላይ አስቀድሞ የተናገረው ነገር ይህ ነው።


ዋናተኛም ሲዋኝ እጁን እንደሚዘረጋ፥ እንዲሁ በመካከሉ እጁን ይዘረጋል፤ ነገር ግን ትዕቢቱን ከእጁ ተንኮል ጋር ያዋርዳል።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios