Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ኢሳይያስ 21:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ጌታም እንዲህ አለኝ፤ “በውል የተቀጠረ ሠራተኛ ቀን እንደሚቈጥር፣ የቄዳር ክብር በአንድ ዓመት ውስጥ ያበቃለታል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ከዚህም በኋላ እግዚአብሔር እንዲህ አለኝ፤ “የሠራተኞች የሥራ ውል እንደሚያልቅ ልክ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ የቄዳር ነገዶች ክብር ይወገዳል፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ገና እን​ዲህ ብሎ​ኛ​ልና፥ “እንደ ምን​ደኛ ዓመት በአ​ንድ ዓመት ውስጥ የቄ​ዳር ልጆች ክብር ሁሉ ይጠ​ፋል፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ጌታ እንዲህ ብሎኛልና፦ እንደ ምንደኛ ዓመት በአንድ ዓመት ውስጥ የቄዳር ክብር ሁሉ ይጠፋል፥

Ver Capítulo Copiar




ኢሳይያስ 21:16
11 Referencias Cruzadas  

የቄዳር መንጎች ሁሉ ወደ አንቺ ይሰበሰባሉ የነባዮትም አውራ በጎች ያገለግሉሻል፤ እኔን ደስ ሊያሰኙ በመሠዊያዬ ላይ ይወጣሉ፥ የክብሬንም ቤት አከብራለሁ።


አሁን ግን ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እንደ ተቀጣሪ ደሞዝተኛ የሞዓብ ክብር፥ ምንም ያህል ሕዝቡ ቢበዛ፥ በሦስት ዓመት ውስጥ ይዋረዳል፤ የሚተርፈውም ሕዝብ እጅግ ጥቂትና ደካማ ይሆናል።”


መኖሪያዬ የራቀ እኔ ወዮልኝ፥ በቄዳር ድንኳኖች አደርሁ።


ዓረብና የቄዳር ልዑላን ሁሉ የእጅሽ ነጋዴዎች ነበሩ፤ በጠቦቶች፥ በአውራ በጎችና በፍየሎች በእነዚህ ከአንቺ ጋር ይነግዱ ነበር።


እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፥ እኔ ጥቁር ነኝ፥ ውብም ነኝ፥ እንደ ቄዳር ድንኳኖች እንደ ሰሎሞንም መጋረጃዎች።


የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ድል ስላደረጋቸው ስለ ቄዳርና ስለ አሦር መንግሥታት፤ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ተነሡ ወደ ቄዳርም ውጡ፥ የምሥራቅንም ልጆች አጥፉ።


ምድረ በዳውና ከተሞቹ የቄዳርም ሰዎች የሚቀመጡባቸው መንደሮች ድምፃቸውን ያንሡ፤ በሴላ የሚኖሩ እልል ይበሉ፥ በተራሮችም ራስ ላይ ሆነው ይጩኹ።


በትውልዳቸው ቅደም ተከተል የተዘረዘሩት የእስማኤል የልጆቹ ስም እንዲህ ነው፥ የእስማኤል የበኩር ልጁ ነባዮት፥ እና ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥


“የሰው ሕይወት በምድር ላይ ብርቱ ሰልፍ አይደለምን? ቀኖቹ እንደ ምንደኛ ቀኖች አይደሉምን?


ትውልዳቸውም እንደዚህ ነው። የእስማኤል በኩር ልጅ ነባዮት፤ ከዚህ በኋላ ቄዳር፥ አድብኤል፥ ሚብሣም፥


ወደ ኪቲም ደሴቶች ተሻገሩና ተመልከቱ፥ ወደ ቄዳርም ላኩና በጣም በጥንቃቄ መርምሩ፥ እነሆ እንዲህ ያለ ነገር ሆኖ እንደሆነ እዩ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios