በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህ ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። በወይንህና በወይራህም ላይ እንዲሁ አድርግ።
ዘዳግም 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) መቼም ቢሆን በምድር ላይ ችግረኛና ድኻ መኖሩ ስለማይቀር፤ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞችህ፥ ለድኾችና ለችግረኖች እጅህን እንድትዘረጋ አዝሃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምድሪቱ ላይ ድኾች ምን ጊዜም አይጠፉም፤ ስለዚህ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞችህ፣ ለችግረኞችና ለድኾች እጅህን እንድትዘረጋ አዝዝሃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መቼም ቢሆን በምድር ላይ ችግረኛና ድኻ መኖሩ ስለማይቀር በአገርህ ለሚገኙ ድኾችና ችግረኞች ጐረቤቶችህ እጅህን እንድትዘረጋ አዝሃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድሃ ከምድርህ ላይ አይታጣምና ስለዚህ እኔ፦ በሀገርህ ውስጥ ላለው ድሃ፥ ለሚለምንህም ወንድምህ እጅህን ዘርጋ ብዬ አዝዝሃለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና ስለዚህ እኔ፦ በአገርህ ውስጥ ላለው ድሀ ለተቸገረው ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ ብዬ አዝዝሃለሁ። |
በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህ ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። በወይንህና በወይራህም ላይ እንዲሁ አድርግ።
ያላችሁን ሽጡ፤ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤
“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ምድር ላይ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ ድኻ ቢኖር፥ በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አትጨክንበት፤ ወይም እጅህን አትሰብስብበት።