ዘዳግም 14:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በየዓመቱ ከእርሻህ ከምታገኘው ምርት ከዐሥር አንዱን እጅ ለይተህ አስቀምጥ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በየዓመቱ ከዕርሻህ ከምታገኘው ምርት ከዐሥር አንዱን እጅ ለይተህ አስቀምጥ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “በየዓመቱ አርሰህ ከምታገኘው ሰብል ሁሉ ከዐሥር እንዱን እጅ ለይተህ ታስቀምጣለህ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ከእርሻህ ዘርተህ በየዓመቱ ከምታገኘው እህልህ ሁሉ ዐሥራት ታወጣለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሻህ በየዓመቱ ከምታገኘው ከዘርህ ፍሬ ሁሉ አሥራት ታወጣለህ። |
በመከርም ጊዜ ፍሬውን ከአምስት እጅ አንዱን እጅ ለፈርዖን ስጡ፥ አራቱም እጅ ለእናንተ ለራሳችሁ፥ ለእርሻው ዘርና ለእናንተ ምግብ፥ ለቤተ ሰዋችሁና ለሕፃናቶቻችሁም ምግብ ይሁን።”
የእህላችንንም በኵራት፥ የእጅ ማንሣታችንን ቁርባን፥ የዛፍ ሁሉ ፍሬ፥ ወይኑንና ዘይቱንም ወደ ካህናቱ ወደ አምላካችን ቤት ጓዳዎች እናመጣ ዘንድ፥ ሌዋውያኑም ከከተሞቻችን እርሻ ሁሉ አሥራት ይቀበላሉና የመሬታችንን አሥራት ወደ ሌዋውያን እናመጣ ዘንድ ማልን።
ሌዋውያኑም አሥራቱን በተቀበሉ ጊዜ የአሮን ልጅ ካህኑ ከሌዋውያን ጋር ይሁን፥ ሌዋውያኑም የአሥራቱን አሥራት ወደ አምላካችን ቤት ወደ ጓዳዎች ወደ ዕቃ ቤት ያምጡት።
በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አስገቡ፤ የሰማያቶችን መስኮቶች ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።
መጀመሪያ ከምታዘጋጁት ሊጥ አንድ እንጐቻ ልዩ ስጦታ የሆነ ቁርባን አድርጋችሁ ታቀርባላችሁ፤ ከአውድማውም እንደ ልዩ ስጦታ አድርጋችሁ እንደምታቀርቡት ቁርባን እንዲሁ ታቀርቡታላችሁ።
የእህልህን፥ የወይን ጠጅህንና የዘይትህን አሥራት፥ ወይም የቀንድ ከብት፥ የበግና የፍየል መንጋህን በኵራት፥ ወይም ለመስጠት የተሳልኸውን ወይም የፈቃድህን ስጦታ፥ ወይም የእጅህን ስጦታ፥ በከተሞችህ ውስጥ መብላት የለብህም።
እዚያም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራታችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ ስእለቶቻችሁንና የፈቃዳችሁን ስጦታዎች፥ የከብት መንጋችሁን እና የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን በኵራት አቅርቡ።