Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሚልክያስ 3:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አስገቡ፤ የሰማያቶችን መስኮቶች ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በቤቴ መብል እንዲኖር፣ እኔንም በዚህ እንድትፈትኑኝ ዐሥራቱን ሁሉ ወደ ጐተራ አስገቡ” ይላል የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር፤ “የሰማይን መስኮት የማልከፍትላችሁ፣ የተትረፈረፈ በረከትንም ማስቀመጫ እስክታጡ ድረስ የማላፈስስላችሁ ከሆነ ተመልከቱ።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 በቤተ መቅደሴ ሲሳይ ይበዛ ዘንድ ዐሥራቴን በሙሉ ወደ ጐተራ አግቡ፤ እናንተ ይህን ብታደርጉ እኔ ደግሞ የሰማይን መስኮቶች ከፍቼ መልካም የሆነውን በረከት ሁሉ አብዝቼ ባልሰጣችሁ በዚህ ልትፈትኑኝ ትችላላችሁ።

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፣ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አግቡ፥ የሰማይንም መስኮት ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።

Ver Capítulo Copiar




ሚልክያስ 3:10
35 Referencias Cruzadas  

ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል፥ ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከዐሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።”


ኖኅ ስድስት መቶ ዓመት በሆነው፥ በሁለተኛው ወር፥ ከወሩም በዓሥራ ሰባተኛው ቀን ላይ፥ ከምድር በታች ያለው የታላቁ ጥልቅ መፍለቂያዎች ሁሉ በድንገት ተነደሉ፥ የሰማያትም መስኮቶች ተከፈቱ፥


ለዚህም ቃል ያ አገልጋዩ የሰጠው መልስ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” የሚል ነበር። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም” ብሎት ነበር።


በዚህ ጊዜ የንጉሡ የቅርብ ባለሟል የሆነ አገልጋዩ ኤልሳዕን፥ “እግዚአብሔር ራሱ የሰማይ መስኮቶችን ከፍቶ እህልን እንደ ዝናብ ቢያዘንብ እንኳ ይህ ሊሆን ከቶ አይችልም!” ሲል በመጠራጠር ተናገረ። ኤልሳዕም “ያን እህል በዐይንህ ታያለህ፤ ነገር ግን ከእርሱ ምንም ነገር አትቀምስም!” አለው።


ከሌዋውያን አኪያ በእግዚአብሔር ቤት በሚሆኑ ቤተ መዛግብትና በንዋየ ቅዱሳቱ ቤተ መዛግብት ላይ ተሾሞ ነበር።


በዚያን ቀን በይሁዳም በአገልጋዮቹ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ስላላቸው፥ የካህናቱንና የሌዋውያኑን እድል ፈንታ እንደ ሕጉ ከከተሞች እርሻዎች ያከማቹ ዘንድ ለእጅ ማንሣት ቁርባንና ለበኵራት ለአሥራትም በየዕቃ ቤቶቹ ላይ በዚያ ቀን ሰዎች ተሾሙ።


እስራኤልም ሁሉ በዘሩባቤልና በነህምያ ዘመን ለመዘምራኑና ለበረኞቹ እድል ፈንታቸውን በየዕለቱ ይሰጡ ነበር፥ የተቀደሰውንም ነገር ለሌዋውያን ሰጡ፥ ሌዋውያኑም ከተቀደሰው ነገር ለአሮን ልጆች ሰጡ።


ትልቅ ለሌዋውያን፥ ለመዘምራን፥ ለበረኞቹ እንደ ሕጉ የተሰጣቸውን የእህሉን ቁርባንና ዕጣኑን፥ ዕቃዎቹንም፥ የእህሉንና የወይኑን የዘይቱንም አሥራት፥ ለካህናቱም የሆነውን የማንሣት ቁርባን አስቀድሞ ያስቀመጡበትን ታላቁን ጓዳ አዘጋጅቶለት ነበር።


በጌታ ታመን፥ መልካምንም አድርግ፥ በምድርም ተቀመጥ፥ ታምነህም ተሰማራ።


ደመናውንም ከላይ አዘዘ፥ የሰማይንም ደጆች ከፈተ፥


ደመናት ዝናብ በሞሉ ጊዜ በምድር ላይ ያፈስሱታል፥ ዛፍም ወደ ደቡብ ወይም ወደ ሰሜን ቢወድቅ፥ ዛፉ በወደቀበት ስፍራ በዚያ ይኖራል።


እነርሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያሉትን ስፍራዎች ለበረከት አደርጋቸዋለሁ፥ ዝናቡንም በጊዜው አወርዳለሁ፤ የበረከት ዝናቦችም ይሆናሉ።


የበኩራቱ ሁሉ መጀመሪያ፥ ስጦታ ሁሉ፥ ስጦታዎቻችሁ ሁሉ፥ ለካህናት ይሆናል፤ በቤትህም ውስጥ በረከት እንዲያድር የሊጣችሁን በኵራት ለካህን ትሰጣላችሁ።


ለዘለዓለምም ለእኔ እንድትሆኚ አጭሻለሁ፤ በጽድቅና በፍርድ፥ በምሕረትና በጽኑ ፍቅር ለእኔ አጭሻለሁ።


ጌታም መልሶ ሕዝቡን፦ እነሆ፥ እህልንና ወይንን ዘይትንም እልክላችኋለሁ፤ እናንተም በእርሱ ትጠግባላችሁ፥ ከእንግዲህም ወዲያ በአሕዛብ መካከል መሰደቢያ አላደርጋችሁም።


አውድማዎችም እህልን ይሞላሉ፥ መጥመቂያዎችም የወይን ጠጅንና ዘይትን አትረፍርፈው ያፈስሳሉ።


ለብዙም ጊዜ በጎተራ የተቀመጠውን ቀድሞ የነበረውን እህል ትበላላችሁ፤ ለአዲሱም ቦታ ለማስለቀቅ ቀድሞ በጎተራ የነበረውን ታወጣላችሁ።


“በሥርዓቶቼ ብትመላለሱ፥ ትእዛዛቴንም ብትጠብቁ ብታደርጉአቸውም፥


“የምድሪቱም አሥራት ሁሉ፥ ከምድሪቱ ዘር ወይም ከዛፍ ፍሬ ቢሆን፥ የጌታ ነው፤ ለጌታ የተቀደሰ ነው።


ዘር በጎተራ አሁንም አለን? ወይንና የበለስ ዛፍ ሮማንና የወይራ ዛፍ አላፈሩም፤ ከዚህች ቀን ጀምሬ እባርካችኋለሁ።


ለሌዊም ልጆች፥ እነሆ፥ በመገናኛው ድንኳን አገልግሎት ስለሚያገለግሉ፥ የእስራኤልን ልጆች አሥራት ሁሉ ርስት አድርጌ ሰጥቼአለሁ።


ነገር ግን አስቀድማችሁ የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን ፈልጉ፥ እነዚህም ሁሉ ይጨመሩላችኋል።


እዚያም የሚቃጠሉ መሥዋዕቶቻችሁንና ሌሎች መሥዋዕቶቻችሁን፥ አሥራታችሁንና የእጃችሁን ስጦታ፥ ስእለቶቻችሁንና የፈቃዳችሁን ስጦታዎች፥ የከብት መንጋችሁን እና የበግና የፍየል መንጋዎቻችሁን በኵራት አቅርቡ።


“በየዓመቱ ከእርሻህ ከምታገኘው ምርት ከዐሥር አንዱን እጅ ለይተህ አስቀምጥ።


ይህን የምታደርገው የራሱ ድርሻ ወይም ርስት የሌለው ሌዋዊና መጻተኛ፥ በከተሞችህ የሚኖሩ አባት የሌላቸውና መበለቶች መጥተው እንዲበሉና እንዲጠግቡ፥ አንተንም አምላክህ ጌታ በእጆችህ ሥራ ሁሉ እንዲባርክህ ነው።


ጌታ መልካሙን መዝገብ ሰማዩን ይከፍትልሃል፤ ለምድርህ በወቅቱ ዝናብን ይሰጣል፤ የእጅህንም ሥራ ሁሉ ይባርካል፤ አንተም ለብዙ አሕዛብ ታበድራለህ፥ አንተ ግን ከማንም አትበደርም።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos