አሞጽ 8:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “በዚያም ቀን፥” ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ “ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለሁ፥ ቀኑም በብርሃን ሳለ ምድሩን አጨልማለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “በዚያ ቀን፣ ፀሓይ በቀትር እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ ምድርንም ደማቅ ብርሃን ሳለ በቀን አጨልማታለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ገና በእኩለ ቀን ፀሐይ እንድትጠልቅ አደርጋለሁ፤ በቀትርም ምድሪቱን አጨልማለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያም ቀን ፀሐይ በቀትር ይገባል፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ብርሃንም በምድር ላይ በቀን ይጨልማል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያም ቀን ፀሐይ በቀትር እንድትገባ አደርጋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ በብርሃንም ቀን ምድሩን አጨልማለሁ። |
ሳትጨልም እግራችሁም በጨለሙት ተራሮች ላይ ሳትሰናከል፥ በተስፋ የምትጠባበቁትን ብርሃን ለሞት ጥላና ለድቅድቅ ጨልማ ሳይለውጠው፥ ለአምላካችሁ ለጌታ ክብርን ስጡ።
ሰባት የወለደች ደክማለች፥ ነፍስዋንም አውጥታለች፤ ቀን ገና ሳለ ፀሐይዋ ገብታባታለች፤ አፍራለች ተዋርዳለችም፤ የተረፉትንም በጠላቶቻቸው ፊት ለሰይፍ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ ይላል ጌታ።”
“እነሆ፥ ተራሮችን የሠራ፥ ነፋስንም የፈጠረ፥ የልቡንም ሐሳብ ለሰው የሚነግር፥ ንጋትን ጨለማ የሚያደርግ፥ በምድርም ከፍታዎች ላይ የሚረግጥ፥ ስሙ የሠራዊት አምላክ ጌታ ነው።”
ሰባቱን ከዋክብትና ኦሪዮን የተባለውን ኮበብ የፈጠረ፥ የሞትን ጥላ ወደ ንጋት የሚለውጥ፥ ቀኑንም በሌሊት የሚያጨልም፥ የባሕሩንም ውኆች ጠርቶ በምድር ፊት ላይ የሚያፈስሳቸው እርሱ፥ ስሙ ጌታ ነው።
ስለዚህ ለእናንተ ራእይ የሌለው ሌሊት ይሆንባችኋል፥ የማትጠነቁሉበት ጨለማ ይሆንባችኋል፤ ፀሐይ በነቢያት ላይ ትጠልቅባቸዋለች፥ ቀኑም ይጨልምባቸዋል።
የማያቋርጥ አንድ የብርሃን ቀን ይሆናል፥ እርሱም በጌታ ዘንድ የታወቀ ይሆናል፤ ቀንም አይሆንም፥ ሌሊትም አይሆንም፤ ሲመሽም ብርሃን ይሆናል።
“ከነዚያ ቀናት መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይሎችም ይናወጣሉ።
ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጉር ጥቁር ሆነች፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነች፤
አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንና የሌሊት ሲሶው እንዳያበራ ተከለከለ።