ሐዋርያት ሥራ 9:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም “ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታም እንዲህ አለው፤ “ሂድ! ይህ ሰው በአሕዛብና በነገሥታት ፊት እንዲሁም በእስራኤል ሕዝብ ፊት ስሜን እንዲሸከም የተመረጠ ዕቃዬ ነው፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ጌታም ሐናንያን እንዲህ አለው፦ “እርሱ ስሜን ለአረማውያን፥ ለነገሥታትና ለእስራኤል ሰዎች የሚያሳውቅ፥ የእኔ ምርጥ መሣሪያ ስለ ሆነ ወደ እርሱ ሂድ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታችንም እንዲህ አለው፥ “ተነሥና ሂድ፤ በአሕዛብና በነገሥታት፥ በእስራኤል ልጆችም ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ አድርጌዋለሁና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታም፦ “ይህ በአሕዛብም በነገሥታትም በእስራኤልም ልጆች ፊት ስሜን ይሸከም ዘንድ ለእኔ የተመረጠ ዕቃ ነውና ሂድ፤ |
እኔ መረጥኋችሁ እንጂ እናንተ አልመረጣችሁኝም፤ አብም በስሜ የምትለምኑትን ሁሉ እንደሚሰጣችሁ፥ እንድትሄዱና ፍሬ እንድታፈሩ ፍሬአችሁም እንዲኖር ሾምኋችሁ።
ከሦስት ቀንም በኋላ ጳውሎስ የአይሁድን ታላላቆች ወደ እርሱ ጠራ፤ በተሰበሰቡም ጊዜ እንዲህ አላቸው “ወንድሞች ሆይ! እኔ ሕዝቡን ወይም የአባቶችን ሥርዓት የሚቃወም አንዳች ሳላደርግ፥ ከኢየሩሳሌም እንደ ታሰርሁ በሮማውያን እጅ አሳልፈው ሰጡኝ።
ነገር ግን በእግዚአብሔር ጸጋ አሁን የሆንሁትን ሆኛለሁ፤ ለእኔም የተሰጠኝ ጸጋ ከንቱ አልሆነም፤ ይልቁን ከሁሉም በላይ በትጋት ሠርቻለሁ፤ ሆኖም ግን እኔ ሳልሆን ከእኔ ጋር ያለው የእግዚአብሔር ጸጋ ነው።
በማገልገል ላይ ያለ ማንም ወታደር፥ ዐላማው ለወታደርነት የመለመለውን ሰው ለማስደሰት እስከሆነ ድረስ፥ እንደ ማናቸውም ሰው በዕለት ተዕለት ጉዳዮች አይጠመድም።
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ናቸው።”