ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።
ሐዋርያት ሥራ 8:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ሕንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሥልጣን የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ ኀላፊ አንድ ኢትዮጵያ ጃንደረባ ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ተነሥቶ ሄደ። እነሆ፤ የኢትዮጵያ ንግሥት የህንደኬ ባለሟልና የሀብት ንብረቷ ሁሉ አዛዥ የሆነ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ አገኘ። ይህም ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ተነሥቶ ሄደ፤ እነሆ፥ አንድ ኢትዮጵያዊ ጃንደረባ ለእግዚአብሔር ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም ሄዶ ነበር፤ ይህ ሰው ሕንደኬ ለተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት ባለሟልና የገንዘብዋ ሁሉ ኀላፊ ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ተነሥቶም ሄደ፤ እነሆም፥ የኢትዮጵያ ንግሥት የሕንደኬ ጃንደረባ ከሹሞችዋ የበለጠ፥ በሀብቷም ሁሉ ላይ በጅሮንድ የነበረ፥ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ነበር፤ እርሱም ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ተነሥቶም ሄደ። እነሆም፥ ህንደኬ የተባለች የኢትዮጵያ ንግሥት አዛዥና ጃንደረባ የነበረ በገንዘብዋም ሁሉ የሠለጠነ አንድ የኢትዮጵያ ሰው ሊሰግድ ወደ ኢየሩሳሌም መጥቶ ነበር፤ |
ንግሥተ ሳባ እግዚአብሔር ለሰሎሞን ስለ ሰጠው አስደናቂ ጥበብ የሚነገረውን ሁሉ ሰማች፤ ስለዚህ አስቸጋሪ በሆኑ ከባድ ጥያቄዎች ልትፈትነው ወደ ኢየሩሳሌም መጣች።
በሸምበቆ ውስጥ ያሉትን አራዊት፥ በአሕዛብ ውስጥ ያሉትን የበሬዎችንና የወይፈኖችን መንጋ ገሥጽ፥ እንደ ብር የተፈተኑት አሕዛብ እንዳይዘጉ፥ ሰልፍን የሚወድዱትን አሕዛብን በትናቸው።
በዚያን ጊዜ ለሠራዊት ጌታ፥ ከረጅምና ከለስላሳ ሕዝብ፥ ከቅርብም ከሩቅም አስፈሪ ከሆነ ሕዝብ፥ ኀያል ከሆነና ከሚገዛ፥ ወንዞችም ምድራቸውን ከሚከፍሉት ሕዝብ ዘንድ ስጦታ ይመጣለታል፤ ስጦታውም የሠራዊት ጌታ ስም ወደሚገኝበት ወደ ጽዮን ተራራ ይቀርባል።
ጌታ እንዲህ ይላል፦ የግብጽ ድካምና የኢትዮጵያ ንግድ ቁመተ ረጅሞችም የሳባ ሰዎች ወደ አንተ ያልፋሉ፤ ለአንተም ይሆናሉ እጆቻቸውም ታስረው ይከተሉሃል፤ በፊትህም ያልፋሉ፥ ለአንተም እየሰገዱ፦ በእውነት እግዚአብሔር በአንተ አለ፥ ከእርሱም ሌላ አምላክ የለም ብለው ይለምኑሃል።
የግመሎች ብዛት፥ የምድያምና የጌፌር ግመሎች፥ ይሸፍኑሻል፤ ከከሳባ የሆኑት ሁሉ ይመጣሉ፤ ወርቅንና ዕጣንን ያመጣሉ፥ የጌታን ምስጋና ያወራሉ።
በመካከላቸውም ምልክት አደርጋለሁ፥ ከእነርሱም የዳኑትን ዝናዬን ወዳልሰሙ፥ ክብሬንም ወዳላዩ ወደ አሕዛብ ወደ ተርሴስ፥ ወደ ፉጥ፥ ወደ ሉድ፥ ወደ ሞሳሕ፥ ወደ ቶቤል፥ ወደ ያዋን፥ በሩቅ ወዳሉ ደሴቶች እልካቸዋለሁ፤ በአሕዛብም መካከል ክብሬንም ይናገራሉ።
“ሂድ፥ ለኢትዮጵያዊውም ለአቤሜሌክ እንዲህ በለው፦ ‘የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሎቼን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያም ቀን በፊትህ ይፈጸማል።
የደቡብ ንግሥት በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነሥታ ትፈርድበታለች፤ የሰሎሞንን ጥበብ ለመስማት ከምድር ዳርቻ መጥታለችና፤ እነሆ ከሰሎሞን የሚበልጥ እዚህ አለ።