ሐዋርያት ሥራ 26:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህንም ደግሞ በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ እኔ ከቅዱሳን ብዙዎችን በወኅኒ አሳሰርኋቸው፤ ሲገድሉአቸውም አብሬ ተቸሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኢየሩሳሌምም ያደረግሁት ይህንኑ ነበር፤ ከካህናት አለቆች ሥልጣን ተቀብዬ ብዙ ቅዱሳንን አሳስሬአለሁ፤ በመገደላቸውም ተስማምቻለሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኢየሩሳሌም ያደረግኹትም ይህንኑ ነበር፤ ከካህናት አለቆች በተቀበልኩት ሥልጣን ከምእመናን ብዙዎቹ ወደ ወህኒ ቤት እንዲገቡ አድርጌአለሁ፤ ሲገድሉአቸውም ከገዳዮቻቸው ጋር ተስማምቻለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ይህንም በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከሊቃነ ካህናትም ሥልጣን ተቀብዬ ከቅዱሳን ብዙዎችን ወደ ወኅኒ ቤት አስገባኋቸው፤ ሲገድሏቸውም አብሬ እመክር ነበርሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህንም ደግሞ በኢየሩሳሌም አደረግሁት፤ ከካህናት አለቆችም ሥልጣን ተቀብዬ እኔ ከቅዱሳን ብዙዎችን በወኅኒ አሳሰርኋቸው፥ ሲገድሉአቸውም አብሬ ተቸሁ። |
በዚያን ቀንም በኢየሩሳሌም ባለች ቤተ ክርስቲያን ላይ ታላቅ ስደት ሆነ፤ ሁሉም ከሐዋርያትም በቀር ወደ ይሁዳና ወደ ሰማርያ አገሮች ተበተኑ።
የሰሙትም ሁሉ ተገረሙና “ይህ በኢየሩሳሌም ይህን ስም የሚጠሩትን ያጠፋ አይደለምን? ስለዚህስ ታስረው ወደ ካህናት አለቆች ይወስዳቸው ዘንድ ወደዚህ አልመጣምን?” አሉ።
የአይሁድ እምነት ተከታይ በነበርኩበት ጊዜ እንዴት እንደ ኖርኩ፥ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ከመጠን በላይ አሳድድና አጠፋ እንደ ነበር ሰምታችኋል፤