ሐዋርያት ሥራ 2:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነቢይ ስለ ሆነ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደማለለት ስለ አወቀ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነቢይ በመሆኑም፣ እግዚአብሔር ከዘሮቹ አንዱን በዙፋኑ ላይ እንደሚያስቀምጥ በመሐላ ቃል የገባለት መሆኑን ዐወቀ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ነገር ግን ዳዊት ይህን የተናገረው ነቢይ ስለ ነበረና እግዚአብሔር ‘ከዘርህ አንዱን በዙፋንህ ላይ አስቀምጥልሃለሁ’ ሲል በመሐላ የሰጠውን የተስፋ ቃል ያውቅ ስለ ነበር ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነቢይ ስለ ነበረ፥ ከአብራኩም የተገኘውን በዙፋኑ እንዲያነግሥለት እግዚአብሔር መሐላን እንደ ማለለት ስለ ዐወቀ፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነቢይ ስለ ሆነ፥ ከወገቡም ፍሬ በዙፋኑ ያስቀምጥ ዘንድ እግዚአብሔር መሐላ እንደ ማለለት ስለ አወቀ፥ |
ከዚያም “ከእናንተ ጋር ሳለሁ በሙሴ ሕግ፥ በነቢያትና በመዝሙርም ስለ እኔ የተጻፈው ሁሉ መፈጸም ይገባዋል ብዬ የነገርኋችሁ ቃል ይህ ነው፤” አላቸው።
“ወንድሞች ሆይ! ኢየሱስን ለያዙት መሪ ስለሆናቸው ስለ ይሁዳ መንፈስ ቅዱስ አስቀድሞ በዳዊት አፍ የተናገረው የመጽሐፍ ቃል ይፈጸም ዘንድ ይገባ ነበር፤
ይህም አስቀድሞ እንደተባለው፥ “ዛሬ ድምፁን ብትሰሙት ልባችሁን እልከኛ አታድርጉ፤” በፊት እንደተባለ፥ ይህን ከሚያህል ዘመን በኋላ በዳዊት ሲናገር “ዛሬ” ብሎ አንድ ቀን እንደገና ይቀጥራል።
እነዚያ ከዚህ በፊት ካህናት የሆኑት ያለ መሐላ ነው፤ እርሱ ግን ከመሐላ ጋር ካህን ሆኖአልና፤ “ጌታ ሐሳቡን አይቀይርም ‘አንተ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት ለዘላለም ካህን ነህ፤’ ብሎ ምሏል፥፥”
እነዚህ በጉን ይወጋሉ፤ በጉም የጌቶች ጌታና የነገሥታት ንጉሥ ስለ ሆነ እነርሱን ድል ይነሣል፤ ከእርሱም ጋር ያሉት የተጠሩና የተመረጡ የታመኑም ደግሞ ናቸው።”