ሐዋርያት ሥራ 16:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ፤” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሷና ቤተ ሰዎቿ ከተጠመቁ በኋላም፣ “በጌታ ማመኔን በርግጥ ከተረዳችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ጥቂት ተቀመጡ” በማለት አጥብቃ ለመነችን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋና በቤትዋ ያሉ ሰዎች ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ፥ “በጌታ የማምን መሆኔን ካረጋገጣችሁልኝ ወደ ቤቴ መጥታችሁ ተቀመጡ” ስትል አጥብቃ ለመነችን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ከቤተ ሰቦችዋ ጋር ተጠመቀች፤ “ለእግዚአብሔር አማኝ ካደረጋችሁኝስ ወደ ቤቴ ገብታችሁ እደሩ” ብላ ማለደችን፤ የግድም አለችን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም ከቤተ ሰዎችዋ ጋር ከተጠመቀች በኋላ፦ “በጌታ የማምን እንድሆን ከፈረዳችሁልኝ፥ ወደ ቤቴ ገብታችሁ ኑሩ” ብላ ለመነችን፤ በግድም አለችን። |
ይህንም ያመጣሁልህን ስጦታዬን ተቀበል፥ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ጎብኝቶኛልና፥ ለእኔም በቂ አለኝና።” በዚህም መልክ ግድ አለው፥ እርሱም ተቀበለው።
አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤
እኔንና መላዋ ቤተ ክርስቲያንን የሚያስተናግደው ጋዩስ ሰላምታ ያቀርብላችኋል። የከተማው ገንዘብ ያዥ ኤራስቶስ፥ ወንድማችንም ኳርቶስ ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
በመመካቴ ሞኝ ሆኜአለሁ! ይህ እናንተ ግድ ስላላችሁኝ የሆነ ነው። እኔ ከምንም የማልቆጠር ብሆን እንኳን፥ ከዋነኞቹ ሐዋርያት በምንም አላንስምና፥ በእርግጥም እናንተ ስለ እኔ መናገር ይገባችሁ ነበር።
በእስራቴም ወንጌልንም መመከቻና መጽኛ በማድረግ ሁላችሁ ከእኔ ጋር በጸጋ ተካፋዮች ስለ ሆናችሁ፥ በልቤ ትኖራላችሁና ስለ ሁላችሁ ይህን ላስብ ይገባኛል።
እንደ ታማኝ ወንድም በምቆጥረው በስልዋኖስ በኩል፥ ልመክራችሁና ጸንታችሁ የምትቆሙበት ይህ እውነተኛ የእግዚአብሔር ጸጋ መሆኑን ልገልጽላችሁ በማለት፥ ይህን አጭር መልእክት ጽፌላችኋለሁ።
እርሱም፥ “አልበላም” በማለት እምቢ አለ። ነገር ግን የራሱ ሰዎች ከሴትዮዋ ጋር ሆነው አጥበቀው ስለ ለመኑት ቃላቸውን ሰማ። ከመሬትም ተነሥቶ በአልጋ ላይ ተቀመጠ።