La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ሳሙኤል 19:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ስለዚህ ንጉሡ ሺምዒን፥ “አትሞትም” አለው፤ ይህንንም ንጉሡ በመሐላ አጸናለት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የሳኦል ልጅ ሜምፊቦስቴም ንጉሡን ለመቀበል ወረደ። ንጉሡ ከተሰደደበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ተመለሰበት ዕለት ድረስ ለእግሩ ተገቢውን ጥንቃቄ አላደረገም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም ነበር።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዚህ በኋላ የሳኦል የልጅ ልጅ መፊቦሼት ንጉሡን ለመቀበል ወረደ፤ ንጉሡ ከኢየሩሳሌም ከወጣበት ጊዜ አንሥቶ አሁን በድል አድራጊነት እስከ ተመለሰበት ጊዜ ድረስ መፊቦሼት እግሩን አልታጠበም፤ ጢሙን አልተላጨም፤ ልብሱንም አላጠበም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

የሳ​ኦ​ልም የልጅ ልጅ ሜም​ፌ​ቡ​ስቴ ንጉ​ሡን ሊቀ​በል ወረደ፤ ንጉ​ሡም ከሄ​ደ​በት ቀን ጀምሮ በሰ​ላም እስከ ተመ​ለ​ሰ​በት ቀን ድረስ እግ​ሩን አላ​ነ​ጻም፤ ጥፍ​ሩ​ንም አል​ቈ​ረ​ጠም፤ ጢሙ​ንም አል​ላ​ጨም፤ ልብ​ሱ​ንም አላ​ጠ​በም ነበር።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

የሳኦልም ልጅ ሜምፊቦስቴ ንጉሡን ሊቀበል ወረደ፥ ንጉሡም ከሄደ ጀምሮ በደኅና እስከ ተመለሰበት ቀን ድረስ እግሩን አልጠገነም፥ ጢሙንም አልቆረጠም፥ ልብሱንም አላጠበም ነበር።

Ver Capítulo



2 ሳሙኤል 19:24
12 Referencias Cruzadas  

በዚህ ጊዜ ዳዊት ከመሬት ተነሣ፤ ከታጠበ፥ ከተቀባና ልብሱን ከለወጠ በኋላ ወደ ጌታ ቤት ሄዶ ሰገደ። ከዚያም ወደ ክፍሉ ገባ፤ በራሱም ጥያቄ ምግብ አቅርበውለት በላ።


ዳዊት ግን እያለቀሰ፥ ራሱን ተከናንቦ፥ ባዶ እግሩን የደብረ ዘይትን ተራራ ወጣ፤ አብሮት ያለውም ሕዝብ ሁሉ እንደዚሁ ራሱን ተከናንቦ እያለቀሰ ተራራውን ይወጣ ነበር።


ከዚያም ንጉሡ፥ “የጌታህ ልጅ የት ነው?” ሲል ጠየቀው። ጺባም፥ “ ‘የእስራኤል ቤት ዛሬ የአባቴን መንግሥት ይመልስልኛል’ ብሎ ስለሚያስብ፥ በኢየሩሳሌም ተቀምጦአል” አለው።


ከዚያም ጺባ ንጉሡን፥ “ጌታዬ ንጉሥ፥ አገልጋዩን ያዘዘውን ሁሉ፥ አገልጋይህ ይፈጽመዋል” አለው። ስለዚህም መፊቦሼት እንደ አንዱ ሆኖ ከዳዊት ማእድ ይበላ ነበር።


“ከዚህም ጋር መረሳት የሌለበት የብንያም ክፍል በሆነችው በባሑሪም ከተማ ውስጥ የሚኖረው የጌራ ልጅ ሺምዒ አለ፤ እርሱ ወደ ማሕናይም በሄድኩበት ቀን በእኔ ላይ የስድብ ውርጅብኝ አውርዶብኛል፤ ይሁን እንጂ በዮርዳኖስ ወንዝ አጠገብ ባገኘኝ ጊዜ እንደማላስገድለው በጌታ ስም ቃል ገብቼለት ነበር፤


ጌታም ሙሴን አለው፦ “ወደ ሕዝቡ ሂድ፥ ዛሬና ነገን ቀድሳቸው፥ ልብሳቸውንም ይጠቡ፤


ወደ ባይት ወደ ዲቦንም ወደ ኮረብታ መስገጃዎችም ለልቅሶ ወጥተዋል፤ ሞዓብ በናባውና በሜድባ ላይ ታለቅሳለች፤ ራሳቸው ሁሉ ተነጭቶአል፥ ጢማቸውም ሁሉ ተላጭቷል።


ጢማቸውን ላጭተው ልብሳቸውንም ቀድደው ገላቸውንም ተልትለው፥ በጌታ ቤት ለማቅረብ የእህል ቁርባንና ዕጣን በእጃቸው ይዘው፥ ሰማንያ ሰዎች ከሴኬምና ከሴሎ ከሰማርያም መጡ።


“ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ሰዎች መጾማቸውን እንዲያዩላቸው ፊታቸውን ይለውጣሉና፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።


እስረኞችን አብራችኋቸው እንደታሰረ ሆናችሁ አስቡ፤ እናንተም በሥጋ እንዳለ እያሰባችሁ የተጨነቁትንም እንደራሳችሁ አስቡ።