La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ኤልዛቤል የመቀበር ዕድል እንኳ አታገኝም፤ የእርሷም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤’” ይህን ሁሉ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወጣቱ ነቢይ በሩን በመክፈት ከዚያ ክፍል ወጥቶ ሸሸ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ኤልዛቤልን ግን በኢይዝራኤል ዕርሻ ውሾች ይበሏታል፤ የሚቀብራትም አይኖርም።’ ” ይህን ተናግሮም መዝጊያውን ከፍቶ ሮጠ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኤልዛቤል የመቀበር ዕድል እንኳ አታገኝም፤ የእርስዋም ሬሳ በኢይዝራኤል ግዛት ውሾች ይበሉታል፤’ ” ይህን ሁሉ ተናግሮ ከጨረሰ በኋላ ወጣቱ ነቢይ በሩን በመክፈት ከዚያ ክፍል ወጥቶ ሸሸ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ኤል​ዛ​ቤ​ል​ንም በኢ​ይ​ዝ​ራ​ኤል እርሻ ውሾች ይበ​ሉ​አ​ታል፥ የሚ​ቀ​ብ​ራ​ትም አታ​ገ​ኝም።” በሩ​ንም ከፍቶ ሸሸ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ኤልዛቤልንም በኢይዝራኤል እርሻ ውሾች ይበሉአታል፤ የሚቀብራትም አታገኝም።’” በሩንም ከፍቶ ሸሸ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 9:10
6 Referencias Cruzadas  

የሶርያም ንጉሥ ባርያዎች እንዲህ አሉት፦ “አምላካቸው የተራሮች አምላክ ነው፥ ስለዚህ በርትተውብን ነበር፥ ነገር ግን በሜዳ ላይ ከእነርሱ ጋር ብንዋጋ በእርግጥ እንበረታባቸዋለን።


ይህን የወይራ ዘይት በራሱ ላይ አፍስስበት፤ ‘አንተ ተቀብተህ በእስራኤል ላይ እንድትነግሥ እግዚአብሔር አዞአል’ ብለህም ንገረው፤ ከዚህም በኋላ በሩን በመክፈት በተቻለ ፍጥነት ከዚያ ስፍራ ተነሥተህ ሽሽ።”


አህያም እንደሚቀበር ይቀበራል፥ ከኢየሩሳሌምም በር ወደ ውጭ ተጐትቶ ይጣላል።”


ኢይዝራኤል፥ ዮቅድዓም፥ ዛኖዋሕ፥


የንጉሡ አገልጋዮች በዕልፍኙ በር ላይ ቆመው ሲጠባበቁ ኤሁድ ርቆ ሄደ፤ ድንጋዮች ተጠርበው በሚወጡበት በኩል ወደ ሴርታ ይም አመለጠ።