2 ነገሥት 21:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እመለክበት ዘንድ ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያበጀውን የአሼራን የተቀረጸ ምስል ወስዶ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ አስቀመጠ፤ ይህም እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፣ “በዚህ ቤተ መቅደስና ከእስራኤል ነገዶች ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘላለም አኖራለሁ” ያለው ስፍራ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በቤተ መቅደሱም ውስጥ የአሼራን ምስል አኖረ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እግዚአብሔር ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “ይህ በኢየሩሳሌም የሚገኘው ቤተ መቅደስ እኔ ለዘለዓለም እመለክበት ዘንድ ከዐሥራ ሁለቱ የእስራኤል ነገዶች ግዛት ሁሉ የመረጥኩት ስፍራ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን፥ “በዚህ ቤት ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እግዚአብሔርም ለዳዊትና ለልጁ ለሰሎሞን “በዚህ ቤት ከእስራኤልም ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘላለም አኖራለሁ፤ |
“ጠላቶቻቸውን ለመውጋት እንዲዘምቱ ሕዝብህን በምታዝበት ጊዜ በየትኛውም ስፍራ ሆነው ወደዚህች ወደ መረጥኻት ከተማና እኔ ለአንተ ወደ ሠራሁት ወደዚህ ቤተ መቅደስ ፊታቸውን መልሰው በሚጸልዩበት ጊዜ፥
“በፊቴ ያቀረብከውን ጸሎትና ልመና ሰምቼአለሁ፤ እርሱም ለዘለዓለም ለስሜ መጠሪያ እንዲሆን የሠራኸውን ቤተ መቅደስ ቀድሼዋለሁ፤ ዘወትርም እጠብቀዋለሁ።
እስራኤላውያንን ከሰጠኋቸው ምድር ተነቃቅለው እንዲባረሩ አደርጋለሁ፤ ስሜ እንዲጠራበት የቀደስኩትንም ይህን ቤተ መቅደስ እተወዋለሁ፤ በየአገሩ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ እስራኤልን መሳለቂያና መዘባበቻ ያደርጓታል።
ስለዚህም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “በእስራኤል ላይ ያደረግኹትን ነገር ሁሉ በይሁዳም ላይ አደርጋለሁ፤ ይኸውም የይሁዳን ሕዝብ ከፊቴ አስወግዳለሁ፤ የመረጥኳትን ከተማ ኢየሩሳሌምንና ስሜ በዚያ ይጠራል ብዬ የነበረውንም ቤተ መቅደስ እተዋለሁ።”
ከዚህም በኋላ ኢዮስያስ ሊቀ ካህናቱን ሒልቅያን፥ ረዳቶቹ የሆኑትን ካህናትና የቤተ መቅደሱን መግቢያ በር ዘብ የሚጠብቁ ተረኞችን ጠርቶ ለበዓልና አሼራ ተብላ ለምትጠራው ሴት አምላክ፥ እንዲሁም ለከዋክብት ማምለኪያ ያገለግሉ የነበሩትን ዕቃዎች ሁሉ ከቤተ መቅደስ ያወጡ ዘንድ አዘዛቸው፤ ንጉሡም እነዚያን ዕቃዎች ሁሉ ከኢየሩሳሌም ውጪ ባለው በቄድሮን ሸለቆ በእሳት አቃጥሎ ዐመዱን ወደ ቤትኤል ወሰደው፤
አሼራ ተብላ የምትጠራውን ሴት አምላክ ምስል ከቤተ መቅደስ ነቅሎ ከከተማይቱ በማውጣት ወደ ቄድሮን ሸለቆ ወስዶ በእሳት አቃጠለው፤ ትቢያ እስኪሆንም አድቅቆ፥ በሕዝብ መቃብር ላይ በተነው።
እንግዶችንም አማልክትና ጣዖቱንም ከጌታ ቤት አራቀ፥ የጌታም ቤት ባለበት ተራራ ላይና በኢየሩሳሌም የሠራቸውን መሠዊያዎች ሁሉ ወስዶ ከከተማይቱ በስተ ውጭ ጣላቸው።
ጌታ ለዳዊትና ለልጁ ለሰለሞን፦ “በዚህ ቤት ከእስራኤል ነገድ ሁሉ በመረጥኋት በኢየሩሳሌም ስሜን ለዘለዓለም አኖራለሁ፤” ባለበት በጌታ ቤት የሠራውን ጣዖት የቀረጸውን ምስል አቆመ።
ለአባቶቻችሁ ከሰጠኋቸው ምድር እነቅላችኋለሁ፤ ለስሜም የቀደስሁትን ይህን ቤት ከፊቴ አርቄ እጥለዋለሁ፥ በአሕዛብም ሁሉ መካከል ምሳሌና መሳለቂያ አደርገዋለሁ።
ነገር ግን ወደ እኔ ብትመለሱ ትእዛዛቴን ብትጠብቁ ብትፈጽሟቸውም፥ ከእናንተ ውስጥ የሆኑ ሰዎች እስከ ሰማይ ዳርቻ ድረስ እንኳ ቢበተኑ ከዚያ እሰበስባቸዋለሁ፥ ስሜ እንዲኖርበት ወደ መረጥሁት ስፍራ አመጣቸዋለሁ።”