2 ቆሮንቶስ 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የኩነኔ አገልግሎት በክብር ከሆነ፥ ይልቁን የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሰዎችን የሚኰንነው አገልግሎት የከበረ ከሆነ፣ የሚያጸድቀው አገልግሎት የቱን ያህል ይበልጥ የከበረ ይሆን! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰዎች የተኰነኑበት አገልግሎት ይህን ያኽል ክብር ካለው ሰዎች የሚጸድቁበት አገልግሎትማ እንዴት እጅግ የበለጠ ክብር አይኖረውም? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኵነኔን ለምታመጣ መልእክት ብዙ ክብር ከተደረገላት የጽድቅ መልእክትማ ምን ያህል ትከብርና ትመሰገን ይሆን? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የኵነኔ አገልግሎት ክብር ከሆነ፥ ይልቅ የጽድቅ አገልግሎት በክብር አብዝቶ ይበልጣልና። |
ሳይገረዝም በእምነቱ ባገኘው የጽድቅ ማኅተም፥ መገረዝን እንደ ምልክት ተቀበለ፤ ሳይገረዙ ለሚያምኑ ሁሉ፥ ለእነርሱም ጽድቅ ሆኖ እንዲቆጠርላቸው አባት ነውና፤
ከሕግ ሥራ የሆኑት ሁሉ ከርግማን በታች ናቸው፤ “በሕግ መጽሐፍ በተጻፉት ሁሉ የማይኖርና የማይፈጽማቸው ሁሉ የተረገመ ይሁን፤” ተብሎ ተጽፎአልና።
በክርስቶስም በማመን በእምነት ላይ የተመሠረተውን የእግዚአብሔርን ጽድቅ እንጂ በሕግ ላይ የተመሠረተውን የራሴ ጽድቅ ሳይኖረኝ፥ በእርሱ እንድገኝ ነው፤
የኢየሱስ ክርስቶስ አገልጋይና ሐዋርያ ከሆነው ከስምዖን ጴጥሮስ፥ በአምላካችንና በመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ጽድቅ ካገኘነው ጋር አቻ የሆነ ክቡር እምነትን ላገኙ፤