2 ቆሮንቶስ 11:29 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚደክም ማን ነው? እኔም አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው? እኔስ አልናደድምን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ደካማ ማን ነው? እኔስ አብሬ አልደክምምን? በኀጢአት የሚሰናከል ማን ነው? እኔስ አልቈጭምን? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ሰው ሲደክም እኔ አብሬው ያልደከምኩት መቼ ነው? አንድ ሰው በኃጢአት ሲሰናከል እኔም ያልተናደድኩት መቼ ነው? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታሞ እኔ የማላዝንለት ማን ነው? በድሎስ እኔ የማልደነግጥለት ማን ነው? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሚደክም ማን ነው፥ እኔም አልደክምምን? የሚሰናከል ማን ነው፥ እኔም አልናደድምን? |
ኧረ ለመሆኑ የምትበሉበትና የምትጠጡበት ቤት የላችሁምን? ወይስ የእግዚአብሔርን ቤተ ክርስቲያን ትንቃላችሁን? ወይስ ምንም የሌላቸውን ታሳፍራላችሁን? ምን ልበላችሁ? በዚህ ነገር ላመስግናችሁን? አላመሰግናችሁም።
ደካሞችን መጥቀም እንድችል ለደካሞች እንደ ደካማ ሆንኩ፤ በሁሉ መንገድ አንዳንዶችን ማዳን እንድችል፥ ከሁሉ ጋር በሁሉ ነገር እንደ እነርሱ ሆንሁ።
ነገር ግን እነርሱ ከወንጌሉ እውነት ጋር በቅንነት እንዳልሄዱ ባየሁ ጊዜ፥ በሁሉም ፊት ኬፋን እንዲህ አልሁት፦ “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ ሳለ እንደ አይሁድ ሳይሆን እንደ አሕዛብ የምትኖር ከሆነ፥ አሕዛብ አይሁድ እንዲሆኑ ለምን ታስገድዳቸዋለህ?”
“ሥራህንና ድካምህን ትዕግሥትህንም አውቃለሁ፤ ክፉዎችንም ልትታገሥ እንደማትችል፥ እንዲሁም ሐዋርያት ሳይሆኑ ‘ነን’ የሚሉትን መርምረህ ሐሰተኞች ሆነው እንዳገኘሃቸው አውቃለሁ፤
ዳሩ ግን ‘ነቢይ ነኝ’ የምትለውን፥ ባርያዎቼንም እንዲሴስኑና ለጣዖት የታረደውን እንዲበሉ የምታስተምረውንና የምታስተውን ያችን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ስለምትላት የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤