2 ዜና መዋዕል 9:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለሰሎሞንም ፈረሶች ከግብጽና ከየአገሩ ሁሉ ያመጡለት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰሎሞን ፈረሶች የመጡት ከግብጽና ከሌሎች አገሮች ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሰሎሞን ከግብጽና ከሌሎች አገሮች ሁሉ ፈረሶችን ያስመጣ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለሰሎሞንም ፈረሶች ከግብፅና ከየሀገሩ ሁሉ ይመጡለት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለሰሎሞንም ፈረሶችን ከግብጽና ከየአገሩ ሁሉ ያመጡለት ነበር። |
አንዱም ሠረገላ በስድስት መቶ፥ አንዱም ፈረስ በመቶ ኀምሳ ሰቅል ብር ከግብጽ ያስመጡ ነበር፤ እነርሱም መልሰው ለኬጢያውያንና ለሶሪያ ነገሥታት ሁሉ ይልኩ ነበር።
ሰሎሞንም ለፈረሶችና ለሰረገሎች አራት ሺህ ጋጥ፥ ዐሥራ ሁለት ሺህም ፈረሰኞች ነበሩት፥ በሰረገሎችም ከተሞች፥ ከንጉሡም ጋር በኢየሩሳሌም አኖራቸው።
ስለ እርዳታ ወደ ግብጽ ለሚወርዱ በፈረሶችም ለሚደገፉ፥ ስለ ብዛታቸውም በሰረገሎች፥ እጅግ ብርቱዎችም ስለ ሆኑ በፈረሰኞች ለሚታመኑ፥ ወደ እስራኤልም ቅዱስ ለማይመለከቱ ጌታንም ለማይፈልጉ ወዮላቸው!