ድስቶቹ፥ መጫሪያዎቹና ጐድጓዳ ሳሕኖቹ፤ ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሑራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለ ንጹሕ ነሐስ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 4:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምንቸቶቹንም መጫሪያዎቹንም ሜንጦዎቹንም ዕቃቸውንም ሁሉ ኪራም-አቢ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለጌታ ቤት ከተሰነገለ ናስ ሠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምንቸቶችን፣ መጫሪያዎችን፣ ሜንጦዎችንና ከእነዚሁም ጋራ የተያያዙ ዕቃዎች። ኪራምአቢ ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ እንዲሆኑ ለንጉሥ ሰሎሞን የሠራለት ከሚብረቀረቅ ናስ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የእግር መታጠቢያዎችን፥ የእጅ መታጠቢያዎችን፥ ጋኖችን፥ የሥጋ ማውጫ ሜንጦዎችንና ኪራም የሠራውን ሥራ ሁሉ ከንጹሕ ናስ ሠርቶ ለንጉሡ ለሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤት አቀረበለት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምንቸቶቹንም መጫሪያዎቹንም ሜንጦዎቹንም ዕቃቸውንም ሁሉ ኪራም ለንጉሡ ለሰሎሞን ስለ እግዚአብሔር ቤት ከለስላሳ ናስ ሠራ። |
ድስቶቹ፥ መጫሪያዎቹና ጐድጓዳ ሳሕኖቹ፤ ለጌታ ቤት አገልግሎት ይውሉ ዘንድ ሑራም እነዚህን ሁሉ ዕቃዎች ለሰሎሞን የሠራለት ከተወለወለ ንጹሕ ነሐስ ነበር።
እነርሱም ምንቸቶችን፥ መጫሪያዎችን፥ መኰስተሪያዎችን፥ የዕጣን ማስቀመጫዎችንና ከነሐስ የተሠሩ የቤተ መቅደሱ መገልገያ ዕቃዎችን ሁሉ ወሰዱ።
ለሜንጦቹና ለድስቶቹ ለመቅጃዎቹም ጥሩውን ወርቅ፥ ለወርቁም ጽዋዎች ወርቁን በየጽዋው ሁሉ በሚዛን፥ ለብሩም ጽዋዎች ብሩን በየጽዋው ሁሉ በሚዛን ሰጠው፤