ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት በጸደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን ከአገልጋዮቹና ከመላው እስራኤል ጋር አዘመተው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ራባ የተባለችውንም ከተማ ከበቡ፤ በዚህ ጊዜ ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።
2 ዜና መዋዕል 36:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደናፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፥ የከበረውንም የጌታን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በጸደይም ወራት ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ከፍተኛ ዋጋ ካላቸው ዕቃዎች ጋራ ወደ ባቢሎን ወሰደው። የዮአኪንን አጎት ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጸደይ ወራት በደረሰ ጊዜ ንጉሥ ናቡከደነፆር ኢኮንያንን እስረኛ አድርጎ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ የቤተ መቅደሱንም ሀብት ዘርፎ ወሰደ፤ ከዚህ በኋላ የኢኮንያን አጎት የሆነውን ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓመቱም ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ የአባቱን የኢዮአቄምን ወንድም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዓመቱ ባለፈ ጊዜ ንጉሡ ናቡከደነፆር ልኮ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ የከበረውንም የእግዚአብሔርን ቤት ዕቃ ከእርሱ ጋር አስወሰደ፤ ወንድሙንም ሴዴቅያስን በይሁዳና በኢየሩሳሌም ላይ አነገሠ። |
ነገሥታት ለጦርነት በሚወጡበት በጸደይ ወራት ዳዊት ኢዮአብን ከአገልጋዮቹና ከመላው እስራኤል ጋር አዘመተው፤ እነርሱም አሞናውያንን አጠፉ፤ ራባ የተባለችውንም ከተማ ከበቡ፤ በዚህ ጊዜ ግን ዳዊት በኢየሩሳሌም ቀርቶ ነበር።
‘የቀድሞ አባቶችህ እስከዚህች ቀን ያከማቹት በቤተ መንግሥትህ ያለው ሀብት ሁሉ ተጠራርጎ ወደ ባቢሎን የሚወስድበት ጊዜ ይመጣል፤ ምንም ነገር አይቀርም፤
የእግዚአብሔርንም ቤት ዕቃ ሁሉ፥ ታላቁንና ታናሹን፥ የጌታንም ቤት መዝገብ፥ የንጉሡንና የሹማምንቱን መዝገብ፥ እነዚህን ሁሉ ወደ ባቢሎን ወሰደ።
የዚህችንም ከተማ ባለጠግነት ሁሉ ጥሪትዋንም ሁሉ ክብርዋንም ሁሉ የይሁዳንም ነገሥታት መዝገብ ሁሉ በጠላቶቻቸው እጅ አሳልፌ እሰጣለሁ፥ እነርሱም ይበዘብዙአቸዋል ይዘውም ወደ ባቢሎን ያመጡአቸዋል።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር የይሁዳን ንጉሥ የኢዮአቄምን ልጅ ኢኮንያንን፥ የይሁዳንም አለቆች ጠራቢዎችንና ብረት ሠራተኞችን ከኢየሩሳሌም ማርኮ ወደ ባቢሎን ካፈለሳቸው በኋላ፥ ጌታ አሳየኝ፥ እነሆም፥ በጌታ መቅደስ ፊት ሁለት ቅርጫት በለስ ተቀምጠው ነበር።
ለካህናትም ለዚህም ሕዝብ ሁሉ እንዲህ ብዬ ተናገርሁ፦ “ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሐሰተኛን ትንቢት ለእናንተ በመናገር፦ ‘እነሆ፥ የጌታ ቤት ዕቃዎች በቅርብ ጊዜ ከባቢሎን ይመለሳሉ’ ብለው ትንቢት የሚነግሩአችሁን የነብዮቻችሁን ቃላት አትስሙ።
የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር ከዚህች ስፍራ ወደ ባቢሎን የወሰዳቸውን የጌታን ቤት ዕቃዎች ሁሉ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደዚህች ስፍራ እመልሳለሁ፤
ለዓመፀኛ ቤት እንዲህ በል፦ እነዚህ ነገሮች ምን እንደ ሆኑ አታውቁምን? በላቸው። ንገራቸው፦ እነሆ የባቢሎን ንጉሥ ወደ ኢየሩሳሌም መጣ፥ ንጉሥዋንና ልዑሎችዋን ወሰደ፥ ከእርሱም ጋር ወደ ባቢሎን አመጣቸው።
በበቀለም ጊዜ ቁመቱ አጭር፥ ሐረጉ ወደ እርሱ የሚመለስ፥ ሥሮቹም በበታቹ የነበሩት ሰፊ ወይን ሆነ፥ ወይንም ሆነ፥ ቅርንጫፎችን አበቀለ፥ ቅጠልም አወጣ።